Get Mystery Box with random crypto!

#በፀጋህ_ተጠቀም 'ሰይጣን ቤተክርስቲያን ሄድሽ አልሄድሽ አይጨንቀውም ፡፡' አሉ የቆሙት እማሆይ | 🇨🇬ደጉ ሳምራዊ የተገፊዎች ድምጽ ✟✟✟

#በፀጋህ_ተጠቀም

"ሰይጣን ቤተክርስቲያን ሄድሽ አልሄድሽ አይጨንቀውም ፡፡" አሉ የቆሙት እማሆይ ፡፡ቀጥለውም፡ "መጽሐፍ ቅዱስም አነበብሽ አላነበብሽ ሰይጣን አይከፋውም ፡፡" አሉ "ታዲያ ሰይጣን የሚጨንቀው እና የሚከፋው መቼ ነው?" ስትል ጠየቀች ሳያት ፡፡ "ቤቴክርስቲያን ሄደሽ የሰማሽውንና መጽሐፍ ቅዱስ አንብበሽ የተረዳሽውን ነገር #መኖር ስትጀምሪ ሰይጣን አብዝቶ ይከፋል ፡፡" አሉ ፡፡

"ልጄ ዋናው ነገር መኖር ነው ፡፡ ያወቅሽውን ካልኖርሽ ሁሉም ነገር ከንቱ ነው ፡፡ የህይወትሽ ቤት አሸዋ ላይ የተገነባ ነው ፡፡ መኖር ስትጀምሪ ግን በማይናወጥ አለት ላይ የተገነባ ህይወት ይኖርሻል ፡፡ ለመኖር ደግሞ በጀመርያ ፈጣሪሺን ከልብ ማክበርና ማፍቀር አለብሽ ፡፡" አሉ የተቀመጡት እማሆይ ደግሞ ፡፡
"ችግሩ የዘመኑ ወጣቶች የአምላክን ፍቅር አታውቁም ፡፡ ልባችሁን የሞላው አለማዊ ነገር ብቻ ነው ፡፡" ሲሏት የቆሙት እማሆይ "ቆይ የፈጣሪ ፍቅር ምን ይመስላል ?" ብላ ጠየቀቻቸው ፡፡

"ይሄውልሽ ልጄ ሰው የሚሰጥሽ ፍቅር ወቅታዊ ነው ፡፡ ገንዘብ ፣ ዝና ፣ ውበት ፣ ሀብት ፣ እውቀትም ሆነ ሁሉም የአለም ነገሮች ከንቱ ናቸው ፡፡ አላፊና ጠፊ ናቸው ፡፡ አንድ የማያልፍ ነገር የፈጣሪ ፍቅር ብቻ ፡፡ ፈጣሪ ራሱ ደሞ ፍቅር ነው ፡፡ ስትቀምሺው በቃ ነፍስሽ እረፍት ታደርጋለች ፡፡ ከእሱ ውጪ ምንም አያምርሽም ፡፡ ልብሽ ቅልጥ ትላለች ፡፡" አሉ የተቀመጡት እማሆይ ፡፡
"ይገርማል!. ....ታድላችኋል!" አለች ሳያት አቀርቅራ ፡፡
"አንቺም እኮ ታድለሻል!" ሲሉ የቆሞት እማሆይ መለሱላት ፡፡ ካቀረቀረችበት ቀና ብላ "ምንድን ነው የታደልኩት ?" ስትል ጠየቀቻቸው ፡፡ "ውበት ነዋ ፡፡ በጣም ውብና ቆንጆ ልጅ ነሽ ፡፡" "ታዲያ ምን ያደርጋል አላፊና ጠፊ ነው አላላችሁም!"

"ቢሆንም እስኪጠፋ ድረስ በተሰጠሽ ጸጋ የማይጠፋ ስራ መከወን አለብሽ ፡፡ እግዚአብሔር ለሁሉም ሰው የተለያየ ጸጋ ስጥቷል ፡፡ ለሙሴ ህግ ለሰለሞን ጥበብ ፣ ለዕዮብ ትዕግስት ፣ ለጳውሎስ መልዕክ ፣ ለማርያም ቅድስና እንደሰጠው ለእኛም የሰጠን ጸጋ አለው ፡፡ እግዚአብሔር ቁንጅና ፣ ስልጣን ፣ እውቀት ፣ ምንኩስና ፣ ድምጽ ወዘተ ነገር ሲሰጠን በአላማ ነው ፡፡" አሉ የተቀመጡት እናት ፡፡

"አላማው ምንድን ነው ?" አሁንም ጠየቀች ሳያት ፡፡ "አላማው በተሰጠን ጸጋ ማገልገል ነው ፡፡ ሰዎችን መርዳት እና በመልካም ስራችን የፈጣሪ ብርሃን በእኛ ውስጥ እንዲያበራ ማድረግ ነው ፡፡ አለምን የተሻለች ቦታ ማድረግ ነው ፡፡ በጎ ስራችንን ሰዎች ተመልክተው ፈጣሪን እንዲያመሰግኑ ማድረግ ነው ፡፡" አሉ እማሆይ ፡፡ "ብዙ ሰው ግን እግዚአብሔር በሰጠው ጸጋ ይጠፋበታል ፡፡ አብዝቶ በዛ እየተመካ ይሰነካከላል ፡፡ ይወድቃል ፡፡ አንቺ እንዴት ነሽ ? በቁንጅናሽ ምን እያደረግሽ ነው ? " ተጠየቀች ሳያት ፡፡

"እንዳላችሁት ባይሆንም በተቻለኝ መጠን በምሰራው ስራ ሰዎችን ለማነቃቃት እጥራለው ፡፡በተለይ የአገሬ ሴቶች የተሻለ ቦታ ደርሰው የማየት ጉጉት አለኝ ፡፡" ስትል መለሰች ፡፡ "አይዞሽ ልጄ ፡፡ ጉጉት ካለሽ መንፈስ ቅዱስ ያሳካልሻል ፡፡ ባንቺ ውስጥ አልፎ የልብሽን መሻት ይፈጽማል ፡፡ ዋናው ነገር ያለው ልብ ላይ ነው ፡፡ እሱ ከጸዳ ሌላው ቀላል ነው ፡፡" አሉ የቆሙት እማሆይ ፡፡

"መጠንቀቅ ያለብሽ ደስታሽን አለማዊ ነገር ላይ እንዳይሆን ነው ፡፡ ሁላችንም በዚህ ምድር ለኮንትራት ህይወት የመጣን ነን ፡፡ ቀናችን ሲደርስ እንሄዳለን ፡፡ እስከዛ ግን ራሳችንን ለዘለዓለማዊው ህይወት ማሰናዳት ይገባናል ፡፡

እሱም ከምንም ነገር በፊት ፈጣሪን አስቀድሞ መኖር ነው ፡፡ በሙሉ አእምሮ ፣ አንደበት ፣ መንፈስና ጉልበታችን ፈጣሪን ካፈቀርን የምድር ህይወት አይከብደንም ፡፡ እንዲሁም ወደ መንፈሳዊው አለም የምንወጣበት ቆንጆ መሠላል ይሆናል ፡፡"
═════════❁✿❁ ═════════
ሠናይ ውሎ!!!


ይቀላቀሉን
@ETHIOPIA_Hagerie