Get Mystery Box with random crypto!

መስቀልን በጉራጌ አዲስ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን Tourism Ethiopia | PAPIO BELETE 💚💛❤️

መስቀልን በጉራጌ አዲስ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን Tourism Ethiopia የምስራች ይለናል። የጥያ ትክል ድንጋይ መገኛ፣ የበርካታ የባህል እሴቶች መፍረቂያ፣ የጥንታዊ ገዳማትና አድባራት እንዲሁም መስጊዶች መገኛ የሆነው ጉራጌ መስቀልና ሌሎች መስህቦች በቱሪስቶች እንዲጎበኙ እና ለማህበረሰቡ የገቢ ምንጭ ለማድረግ የማስተዋወቅ ስራ እየተሰራ ይገኛል።

ሰሞኑን ከተለየዩ ሀገራት የመጡ የውጭ ሀገር ዜጎች በጉራጌ በምሁር አክሊል በመገኘት "ራይድ ዘሪፍት የተሠኘ የብስክሌት ውድድር ፕሮግራምና በመስቀል በዓል ስርዓት ላይ ተሳትፎ አድርገዋል። ቱሪስቶቹ በዋቤ ወንዝ ላይ የጀልባ ላይ ቀዘፋ፣ በሐዋርያት ተራራማ አካባቢ የብስክሌት (Mountain bike tour) ጉዞም አድርገዋል፡፡ ዳይናስቲ ኢትዮጵያ፣ ተስፋ ቱር እና ሰሜን ኢኮ ሳይክሊንግ ቱር አስጎብኝ ድርጅቶች ከቱሪዝም ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ይህ የቱሪስቶቹ ቆይታ በቆቀር ቀበሌ በተለያዩ ቤተሰቦች በመገኘት በጉራጌ ማኅበረሰብ ዘንድ በታላቅ ባህላዊና ሃይማኖታዊ ስርዓት በሚከበረው የመስቀል በዓል ስርዓት ላይ ተሳትፈዋል፡፡
.
via...ግሩም