Get Mystery Box with random crypto!

... __ልሂድ ያልከኝ ለታ እንዴት ነሽ ስትለኝ ያኔ የመለስኩልህ ከሌለህ የለሁም ብዬ የነገ | የፍቅር ደብዳቤ



...
__ልሂድ ያልከኝ ለታ

እንዴት ነሽ ስትለኝ ያኔ የመለስኩልህ
ከሌለህ የለሁም ብዬ የነገርኩህ
እንዳትረሳኝ ብዬ ዛሬም ደገምኩልህ

እውነቴን ነው ፍቅሬ ከሌለህ የለሁም
አንተ ስላለከኝ አሁን ላይ አልሞትኩም
ግን ውዴ ካጣሁክ በህይወት እያለው
አልቅሰህ ሳትቀብረኝ በቁሜ እሞታለው

እስኪ አስበው ውዴ በቁም ከሞትኩብህ
አላቅፍህ አልስምህ ግጥም አልፅፍልህ
ባካል አላገኝህ ወይ አልደውልልክ
ያለሁበት ጠፍቶኝ ስንከራተትልህ

አንተ የሄድክ ጊዜ ገነትንና ሲኦልን እዚው አየዋለው
ገነትን በትዝታ ሲኦልን በእብደት ውስጥ እመለከታለው

ስለዚህ ፍቅሬ ሞቴ ያማረህ ጊዜ ምንም እንዳትለኝ
3 ፊደል ተናግረህ "ልሂድ"ብቻ በለኝ
..
:¨·.·¨: ❀
·. ┈┈••◉❖◉●••┈
  ይ ላ ሉን! ➢
@efrem_seyum