Get Mystery Box with random crypto!

#ያሜናዳብ #ክፍል_ሰባት ጆን አ/አ ልሂድ አንድ መጨረስ ያለብኝ ጉዳይ አለ ሁለት ቀን በኋላ | የፍቅር ደብዳቤ

#ያሜናዳብ

#ክፍል_ሰባት


ጆን አ/አ ልሂድ አንድ መጨረስ ያለብኝ ጉዳይ አለ ሁለት ቀን በኋላ እመለሳለሁ ሲለኝ ወገቤ ቁምጥ አለ በቃ ምለው ሁላ ጠፋኝ እንደ ምንም ብዬ እሺ ዛሬ እኔ ጋር
ዋል አልኩት ትንሽ ካቅማማ በኋላ እሺ በቃ ግን ማታ ላይ እሄዳለሁ አለኝ ደስ ብሎኝ እሺ አልኩ በቃ ጆን ካየሁበት ቀን ጀምሬ ብዙ ጓደኞቼ ጋር ተላያይቻለሁ ድሮ ያሉበት ድረስ እሄድ ነበረ እሱ ከመጣ በኋላ ግን አይደለም እነሱ ዘንድ ልሄድ ይቅርና ፈልገውኝ ራሱ አጡኝ ድንገት
ስደውልላቸው ዛሬ ከየት ትዝ አልንሽ
ወይስ ምንድ ነው ጉድ ኤልሲ የነገረችን ነገር እውነት ነው እንዴ አሉ ሙድ እየያዙብኝ እሱን ተውትና የት ነው ያላቹ ስላቸው አዶቭ ካፌ ነን አሉ ጆንን ይዤው ሄድኩ ልክ እንደ ደረስን ሲያዩን ጓደኞቼ ጆንን ሲያዩ ሁሉም ፀጥ አሉ በቃ ግርምትም አለ ብቻ ስሜታቸውን ለመግለፅ ትንሽ አንገራገራቸው ሁሎችንም አስተዋወኩት እናቴ ሰደውልልኝ ከነሱ ትንሽ ራቅ አልኩኝ ትንሽ ቆይቼ ስመለስ ጆን በሳቅ ሊገላቸው ነው ከምንም በላይ ደግሞ ደንግጬ የቆምኩ አመለ ምትባል ጓደኛችን ስትስቅ ሳያት ነው በህይወቴ አንድም ቀን አይደለም ስትስቅ ፈገግ ስትል እንኳ አይቻት አላውቅም ይሄ ልጅ ምን አስነካት አልኩኝ እኔ ብቻ አደለም እነሱም አስገርሟቸዋል ምንም አይነት ቀልድ አያስቃትም ብቻ የዛሬው ሁኔታዋ በጣም ተለየብኝ በዚህ መሀል ኤልሲ ከሩቅ ስትመጣ አየኋት ልክ ጆንን ስታይ ቆመች በቃ እንደ ምናምን
አደረጋት በኮሪደሩ ጥግ ይዛ መጣችና በጆን ጀርባ ሂዳ ግጥም አድርጋ ጉንጩን ሳመችው የእውነት ለመናገር በጥፊ ብላት ደስታዬን አልችለውም አንቺ ውልብልብ አላት ብናደድም ሳቄን ግን
አልቻልኩም በዚህ መሀል አጠገቤ የተቀመጠች ጓደኛዬ ወደ ጆሮዬ ጠጋ ብላ ዘንድሮ በለስ ቀንቶሻል ደግሞ ስትፈዢ አስበይው አሉሽ አለችኝ አሳቀችኝ የእውነት በቃ ወደ ውሰጤ ተመለከትኩ ልቤ ያለ እሱ ባዶ ሁና አገኘኋት ብቻ ፈጣሪ ይርዳኝ ምን ብዬ እንደ ምነግረው ሳስብ እንኳ ይጨንቀኛል ቀኑን ሙሉ እኛ ጋር ዋለ ጓደኞቼ የማይጠይቁት ጉድ የለም እሱም ለመመለስ ደከመኝ አይልም በዛ ላይ በቃ ጆን ማለት ልዩ ሰው ነው አብረን ውለን ልክ ቤት እንደ ገባን ትንሽ ሻንጣ ነገር ይዞ ወጣ እኔስ ምሆነው አጣሁኝ ጩሂ ጩሂ አለኝ ግን አትሂድ
ማለት አልችልም እናቴ በስተ ጀርባ ነበርች ቻው ብሏት ወጣ የክላሱን ቁልፍ ሰጠኝና ነገ እንድታፀጂው አለ እየሳቀ በይ ቻው ሲለኝ እንባዬ ሲተናነቀኝ ይታወቀኛል በሩ ዘንድ ደርሶ ተመልሶ ሲመጣ እንባዬ ይፈሳል እንቺ ያምሻል እንዴ ሁለት ቀን እንጂ ሁለት አመት እኮ አላልኩም ብሎኝ ግንባሬን ስሞኝ ሄደ ኡፍ ምን አለ የወዱት ሰው ለደቂቃ ባይለዩት አልኩ በልቤ ክላሴ ገብቼ ተኛሁ በቃ ከዛን ቀን በኋላ ጆን በጣም ነበር የናፈቀኝ ሁለት ቀን ሞላ ግን አልመጣም እኔስ ምሆነው አጣሁኝ ትዝ ሲለኝ የክላሱን ቁልፍ ሰጦኛል ቁልፉን ፈልጌ አግቼ እንደ ምንም ሩጬ ክላሱ ገባሁ ቦርሳ ውስጥ ያለውን ሹራብ ሳወጣው ምንም ነፍስ የለኝም በቃ እንደ
እስትፋንስ አፍንጫዬ ጭምቅ አደረኩት ውስጤ ግን እኮ በስንቱ ታዝቦኛል በቃ ጠረኑ ወደ ውስጤ ሲገባ ፈጣሪ የሚያውቀው በቃ እኔ ጋር ያለ መሰለኝ ጆን ይመጣል ብዬ ዛሬ ነገ ብልም የለም ሳምንት ሆነው ሳይመጣ....

ይቀጥላል