Get Mystery Box with random crypto!

ያሜናዳብ #ክፍል_ስድስት እጅህ ላይ አለ አሁን አለችው የለም ግን ደብዳቤው ያለው እኮ te | የፍቅር ደብዳቤ

ያሜናዳብ

#ክፍል_ስድስት

እጅህ ላይ አለ አሁን አለችው የለም ግን ደብዳቤው ያለው እኮ texas ነው አለ
ልቤ ለሁለት ስንጥቅ አለ የፈራሁት ደረሰ ልቤ ደንግጧል ምክንያቱም ጆን ውጭ ሀገር እንደ ሚኖር ብጠረጥርም እርግጠኛ አልነበርኩም አሁን ግን
ከአንደበቱ ሰማሁ አሜርካ ማለት ለእኔ ከምንም በላይ ነው እስትፋንሴ እስኪ መስል ድረስ ነው የተመኘሁት ፌቨንን ምሳ ጋብዘናት ምናምን መጨረሻ ላይ
ተሰናብተናት ቀጥታ ወደ ባ/ዳር በረራ አለ ተብሎ ሀዋሳ ኤርፖርት ውስጥ ነን እኔ ትኬቱን መቼ ነው የቆረጠ እላለሁ ግን እሱ በኦንላይን ኢንተርኔት ጨርሶታል በዚህ መሀል ወደ ባ/ዳር እንደ ገባን እሱ ኩንትራት የያዘው ሹፌር ነበር እየጠበቀን ነው እኔ ግራ የገባኝ መቼ ደውሎ እንደ ጠራው ነው ትኬት ሲቆርጥ አልጋ ሲይዝ
በቃ ብዙ ነገሮችን ሲያደርግ አላየውም ግን ተደርጎ አየዋለሁ እቤት እንደ ደረስን አክስቴን ሰላም ብሏት ወደ ክፍሉ ሄደ እናቴ ቤት የለችም ክላሴ ውስጥ ተኝቼ ሁሉም ነገር እየገረመኝ ነው በቃ እሱ ጋር በአንድ ቀን ውስጥ ይሄን ታክል ስንቀራረብ ከምንም በላይ ነው ደስ ያለኝ
ቢጃማ ለብሼ ኤድፎኔን ሰክቼ በረንዳ ላይ ቁጫ አልኩ እሱም ጃኬት ነገር ደርቦ ወጣ ስንተያይ ፈገግ አለ ትዙ ሻይ ቡና አለኝ አመስግናለሁ አልኩ ግድ የለም እንደ ትናቱ አትሆኚም አለኝ ሳቄን
ለቀኩት ይዘህልኝ ና አልኩ እረ ባክሽ ከፈልግሽ አትመጪም ብሎ ነይ ቶሎ
ነው ምመለስ ብሎ ወጣ የእውነት ለመናገር ልቤ አብሮት ወጣ በቃ አስጠላኝ ከእሱ ለደቂቃም ቢሆን
መለየትን አልፈልግም በፍቅር እንደ ወደኩ አውቂያለሁ ግን በቃ ምሆነው አጣሁኝ እስኪ መጣ ብዬ ተኛሁኝ ከደቂቃዋች በኋላ እናቴ መጣች ስታየኝ ደስ አላት
የሄዳቹበት ጉዳይ ተሰካላቹ አለች አዋ አልኳት እና ጆን የት ሄደ አለች አሁን
ቅርብ ሰአት ነው የወጣ እልኳት ሀሳቤ ጆን ላይ ነው ብቻ በቃ አላውቅም ትንሽ ጋደም እንዳልኩ እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ ለራት ነው ያስነሱኝ ወጥቼ የጆንን ክላስ ሳየው መብራቱ በርቷል በቃ የእውነት ለመናገር በሰአታት ውስጥ ናፍቆኛል ቀጥ ብዬ ወደ ክፍሉ ሄድኩ ሳንኳኳ አቤት አለ ገርበብ አድርጎ ነበር የዘጋው ገባሁኝ እንደ ልማዱ ቁምጣ ለብሶ ወንበሩ ላይ እግሩን ዘርግቶ ለፕቶፑን ይነካካል ትዙዬ አለኝ እቤቱ ግቢያችን አልመስለኝ አለ ሲበዛ በጣም ይስባል ብዙ ዕቃ የለውም ግን ያሉት
የዕቃዋች አቀማመጥ በጣም ልዩ ነው አክስቴ ከውጭ ስትጠራኝ ሰምቼ ወጣሁ ወደ ላይ ቤት ስሄድ ቡና ተፈልቷል
አክስቴ ጆንን ጠራችው ሆነ ብዬ ወደ ውስጥ ገባሁና ጆን ሲመጣ ጠብቄ እራቴን ይዤ ወጣሁ ጆን ጋር ቁጭ አልኩ
እኔ እልበላም አለ ማን ብላ አለህ አልኩ ሳቀብኝ እናቴ ከውስጥ ስትመጣ አንቺ ብላ አትይውም ምን ሆንሽ አለችኝ
አልበላ አለኝ አልኳት የግዱን በላ በቃ እያጎረሰኝ ነው የጨረሰ ነገውን ጆን አ/አ ልሂድ አንድ መጨረስ ያለብኝ ጉዳይ አለ ሁለት ቀን በኋላ እመለሳለሁ ሲለኝ ወገቤ ቁምጥ አለ…

ይቀጥላል
ከ 20 like በኋላ ይቀጥላል