Get Mystery Box with random crypto!

ሶሊያና ( ኤፍሬም ስዩም ) ----------------------------------- ፧ እኔን | የፍቅር ደብዳቤ

ሶሊያና

( ኤፍሬም ስዩም )
-----------------------------------

እኔን ከወንበር ላይ
ቀን ያየሁት እንባ
ቀን ያየሁት ደባ
እንቅልፍ አሳጥቶኝ
ወረቀት ላይ ወስዶኝ
……
እርሷን ካልጋችን ላይ
እንቅልፍ አሽኮርምሟት
ቀን ያየችው ሁሉ በቅዠት አልፎላት ……
እኔ ከቃላት ጋር ጦርነት ገጥሜ
በሰው ልጆች ጭንቀት እጅግ ተዳክሜ
በሌሊት ጭንቀቴ የቀን ስቃይ ላበርድ
ከደጋው ሃሳቤ በረሃ ስሰደድ
እንባን በፊደላት …
ፊደልን በቃላት…
ቃላትን በሃሳብ ወረቀት ላይ ልወልድ
ወረቀት ላይ ፅፌ ወረቀቱን ስቀድ …
እንዲህ እየፃፍኩኝ እያሰብኩኝ ሳለሁ
‹‹የኔ ነሽ›› የምላት …‹‹ያንተ ነኝ››
የምትል
ፍቅሬ ሶሊያና ተናገረች መሰል በቅዠቷ
መሃል …
‹‹ተመልከት ወዳጀ እኔም ካልጋየ ላይ
አንተን በመናፈቅ በስሜት ስሰቃይ ››
ቀ…ና ብየ ባያት እውነት አለው ቃሏ
ፍም መስሏል አካሏ
ከሌሊት ልብሶቿ ጡቷ ሾልኮ ወጥቷል
እጇ ተዘርግቶ እግሯ ተከፋፍቷል
እኔን በመጓጓት ደሟ ጠቆጥቶ
ፍቅሯ ተሰውቶ
ስሜቷ ተጎድቶ
አንዳች ነገር አይቶ እንደፈራ ህፃን
ፊቷ ሲሸማቀቅ ፀጉራ ሲበታተን …
ካ,ልጋው ላይ ተፅፎ አየሁት እውነቷን
ፍ...ቅ...ሬ ሶ...ሊ...ያ...ና አወራችኝ መሰል
በቅዠቷ መሃል …
አስተውል ወንድሜ …
ባንተ የቀለም ቅብ በድርሰትህ አለም
የሰዎች ጥላ እንጅ አካላቸው የለም !
ባንተ ከንቱ ድርሰት በወረቀትህ ላይ
የሰው እንባ ሳይሆን ያንተው ነው የሚታይ
በሌሊት ትጋትህ በድርሰት በግጥም በቀለም ሸራህ ላይ
እኔ ውበቱ ነኝ በፍቅርህ ስሰቃይ
ይህ ሁሉ ቢሆንም
ይህ ሁሉ ቢሆንም . . . ወዲህ እንዳትመጣ
በሌሊት ትጋትህ ሃዘን ሳይቀጣ
በ,ኔ ያልጋ ድርሰት ቅፅበታቶች አሉ
ከየሰው አለም የሚመሳሰሉ
ባንተ ቀለም ሸራ በድርሰትህ ፅሁፍ
ዘመን ይታየኛል እኔን የሚያሳልፍ
ይህ ሁሉ ቢሆንም …
የሰወችን እንባ አትፃፍ ግዴለም
የፍጥረትን ሃዘን ስለህ አትዘልቅም
እውነት አለው ብለህ ሃዘንን አታልም
((ያለቀሱም ሰዎች ሃቀኞች አይደሉም ))
ይልቅ የኔን ስሜት ያንተንም እንባዎች
ሁለቱን አሳየኝ
በድርሰት
በግጥም
በቀለም ሸራህ ላይ እኔን ብቻ ሳለኝ !
እኔን ብቻ ፃፈኝ !
‹‹ያልተደሰተች ሴት›› በሚል መፅሃፍህ
ዘ...ላ...ለ...ም አሻግረኝ
ዘ...ላ...ለ...ም ውሰደኝ
ዘ...ላ...ለ...ም አኑረኝ
‹‹የኔ ነሽ›› የምላት …‹‹ያንተ ነኝ››
የምትል
ፍቅሬ ሶሊያና ተናገረች መሰል በቅዠቷ
መሃል …
t.me/efrem_seyum