Get Mystery Box with random crypto!

ወሃቢያዎች እና ለአላህ ‘አስማእ ወ ሲፋት’ን ማፅደቅ በሚል የሚደሰኩሩት የተመረዘ እሳቤ! •┈┈┈• | Ethiomewlid ኢትዮ መውሊድ

ወሃቢያዎች እና ለአላህ ‘አስማእ ወ ሲፋት’ን ማፅደቅ በሚል የሚደሰኩሩት የተመረዘ እሳቤ!
•┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈•
# ደፍዑ_ሹበሂ_ተሽቢህ (1)
ምስጋና ለተጥራራው ጌታችን አላህ ይሁን። ሰላትና ሰላም በውዱ በሰይዳችን ላይ ይሁን። በመቀጠል፤
አሏህ እንዲህ ብሏል፤
{ ﺍﻟﺮَّﺣْﻤَٰﻦُ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟْﻌَﺮْﺵِ ﺍﺳْﺘَﻮَﻯٰ { ‏[ ﻃﻪ 5 : ]
«አል ረህማን ዓርሽን የተቆጣጠረው ነው» ጣሀ 5
ማንኛውንም ልቡ ያልታወራ ጤናማ ሙስሊም ይህንና ይህን የመሰሉ አንቀፆችን ሲሰማ ቆም ይላል! ,,, አላስፈላጊ እሳቤዎችን ከማሰብ ይቆጠባል። አንቀፁ ለአሏህ የጉድለት እና መመሳል ትርጉም ከማስተላለፍ ፈፅሞ የራቀ መሆኑን ጠንቅቆ ያውቃል።
ነገር ግን ዝንባሌውን በመከተል የተጠመደ አመሳሳይ ከሆነ፤
☞ "ሰማያት አሏህን ተሸክመዋል" ፣
☞ "አላህን ፍጥረታቱ ያካብቡታል"፣
☞ "አላህ ከዓርሽ ፈላጊ ነው" ወይም
☞ "አሏህ ዐርሽ ላይ ተቀምጧል/ ተደላድሏል"
☞ "አርሽ በላይ ከፍ ብሎ ተንሳፏል"
የሚሉ መጥፎ መልዕክቶችን ሊረዳ ይችላል፤ አላህ ማስተዋል የነፈገው ከሆነ።
◆ነገር ግን አሏህ የመራው፦
ኢማሙ ሻፊዒይ እንዳሉት ሁሉ
" ﺃﻣﻨﺖ ﺑﻼ ﺗﺸﺒﻴﻪ ﻭﺻﺪﻗﺖ ﺑﻼ ﺗﻤﺜﻴﻞ .."
"ያለ ምንም ማመሳሰል እን ተሽቢህ አምኜያለው" ሊል ይገባል
እንዲሁም ኢማም አሕመድ እንዳሉት፦
" ﺍﺳﺘﻮﻯ ﻛﻤﺎ ﺃﺧﺒﺮ ﻻ ﻛﻤﺎ ﻳﺨﻄﺮ ﻟﻠﺒﺸﺮ
"ኢስተዋ አሏህ በጠቀሰው መልኩ እንጂ በሰው ልጅ አይምሮ ከሚሳለው አተረጎገም የፀዳ ነው"
ኢማም አሕመድ ይህን ያሉበት ምክኒያት፡
ይህንን ቃል ﺍﺳﺘﻮﻯ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻌﺮﺵ የሚለውን
ለሰው/ ለፍጡር ስንጠቀመው የሚያስረዳው ትርጉም ለአሏህም ያንን ቃል በመጠቀም ስንገልፀው ለፍጡር በምንጠቀመው አገላለፅ ፈፅሞ እንዳንቶረግመው ለማስጠንቀቅ ሲባል ነው።
ለምሳሌ፦
ﻓﻼﻥ ﺍﺳﺘﻮﻯ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻌﺮﺵ
"አከሌ አርሽ ላይ ኢስቲእ አደረገ" ቢባል
ኢስተዋ የሚለው ብዙ ትርጉም የያዘ ቢሆንም በቀጥታው የምንረዳው ያ ሰውዬ "ዙፋን ላይ መደላደሉን ነው" !
ልብ ልንለው የሚገባው ግን ይህ አተሮጋገም መደላደልም ሆነ መቀመጥ ለሱ መገለጫ እና ተገቢ ለሆነለት (ለፍጡር) ነው።
በዐረበኛ ቋንቋ ይህንኑ ቃል ለንጉስ ስንጠቀመው ግን,, ከአካላዊ ትርጓሜ ባሻገር የተለየ ቁም ነገርን ያዘለ ቃል ይሆናል። ማለትም ስልጣን መያዙንና ንግስናውን የሚያመላክት ነው ዙፋን ላይ መቀመጡ ባይረጋገጥ እንኳ።
✧የአረበኛ ቋንቋ ምሁር ኢማም አልፈዮሚይ እንዲህ ይላሉ፡
ﺍﺳﺘﻮﻯ ﻋﻠﻰ ﺳﺮﻳﺮ ﺍﻟﻤﻠﻚ : ﻛﻨﺎﻳﺔ ﻋﻦ ﺍﻟﺘﻤﻠﻚ ﻭﺇﻥ ﻟﻢ ﻳﺠﻠﺲ ﻋﻠﻴﻪ
"በንግስና ዙፋን ላይ ተቀመጠ ሲባል ባይቀመጥበትም እንኳን ስልጣንን መጎናፀፉን ለማመላከት ነው።"
ስለዚህ ይህንን አንቀፅ በጥሬው ቀጥተኛውን ትርጉም በመያዝ ለመተርጎም መጣደፍ አደገኛ እና የጥሜት አካሄድ መሆኑ ታውቆ እጅጉን ሊወገዝ ይገባል። [አሏህ ከሃዲዎች ከሚሉት ሁሉ የጠራ ነው።]
በዚህና መሰል አሻሚ አንቀፆች ዙሪያ ልንይዘው የሚገባ አቋም አሏህን ከጉድለት፣ ከመመሳሳል ፣ እንዲሁም ከፍጡራን አገላለፅና አካላዊ ትርጓሜ ከማጥራት ጋር ለርሱ ልእልና በሚገባ መልኩ ማፅደቁ ግዴታ ነው።

✧ ኢማም አቡ ሐኒፋ እንዲህ ይላሉ፦
ﻭﻧﻘﺮ ﺑﺄﻥ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻌﺮﺵ ﺍﺳﺘﻮﻯ ﻣﻦ ﻏﻴﺮ ﺃﻥ ﻳﻜﻮﻥ ﻟﻪ ﺣﺎﺟﺔ ﺇﻟﻴﻪ ﻭﻻ ﺍﺳﺘﻘﺮﺍﺭ ﻋﻠﻴﻪ ﻓﻠﻮ ﻛﺎﻥ ﻣﺤﺘﺎﺟﺎ ﺇﻟﻰ ﺍﻟﺠﻠﻮﺱ ﻭﺍﻟﻘﺮﺍﺭ ﻓﻘﺒﻞ ﺧﻠﻖ ﺍﻟﻌﺮﺵ ﺃﻳﻦ ﻛﺎﻥ ﺍﻟﻠﻪ؟ ! ﺗﻌﺎﻟﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻦ ﺫﻟﻚ
«አሏህ በአርሽ ላይ ኢስቲዋእ ማድረጉን እናረጋግጣለን፤ (ኢስቲዋኡ) በአርሽ ፈላጊ ሳይሆን ፤ በርሱ ላይም ሳይደላደል ነው። ከመቀመጥ እና ከመደላደል ፈላጊ ቢሆን ኖሮ ከዐርሽ በፊት ዬት ነበረ ሊባል ነው?! አሏህ ከዚሁ የላቀ ነው!።» [አል ወሲያ ገፅ /70]

✧ኢማም አልበይሀቂይ እንዲህ ይላሉ፦
ﻳﺠﺐ ﺃﻥ ﻳُﻌﻠﻢ ﺃﻥ ﺍﺳﺘﻮﺍﺀ ﺍﻟﻠﻪ ﺳﺒﺤﺎﻧﻪ ﻭﺗﻌﺎﻟﻰ ﻟﻴﺲ ﺑﺎﺳﺘﻮﺍﺀ ﺍﻋﺘﺪﺍﻝ ﻋﻦ ﺍﻋﻮﺟﺎﺝ ، ﻭﻻ ﺍﺳﺘﻘﺮﺍﺭ ﻓﻲ ﻣﻜﺎﻥ ، ﻭﻻ ﻣﻤﺎﺳﺔ ﻟﺸﻲﺀ ﻣﻦ ﺧﻠﻘﻪ ، ﻟﻜﻨﻪ ﻣﺴﺘﻮ ﻋﻠﻰ ﻋﺮﺷﻪ ، ﻛﻤﺎ ﺃﺧﺒﺮ ﺑﻼ ﻛﻴﻒ ، ﺑﻼ ﺃﻳﻦ ،
«ግዴታ መታወቅ ያለበት የአሏህ ኢስቲዋእ ከጠምዛዘነት መስተካከል እንዳልሆነ ፣ በቦታ መደላደልም እንዳልሆነ፣ ከፍጥረቱ ኣንዱም ጋር በመነካካትም እንዳልሆነ ነው። ነገር ግን በዐርሹ ላይ ኢስቲዋእን ኣደረገ ፤ እርሱ ባሳወቀን መልኩ ያለ ከይፊያ(እንዴታ) ፣ ያለ ቦታ » [አል ኢዕቲቃድ] ገፅ/72

የአሏህን "አስማእ እና ሲፋት" እናፀድቃለን በሚል ስለ አላህ የሚነገሩ እውነታዎችን ሁሉ ፍጡራን ላይ በሚያዩቸው ግንዛቤዎች የሚተረጉም እውር አስተሳሰብ ነው። አላህ ይጠብቀን!
በዚህም "ኢስባት" ማድረግን የግድ በአካላዊ ትርጓሜ ከልሆነ በስተቀር አይሆንም የሚል የጥሜታዊ አስተሳሰብ ነው።
በአንቀፁ ላይ የወረደ ቃል ብዙ ትርጉሞችን ያዘለ (ሙተሻቢህ) ሆኖ ሳላ በቀጥተኛው ካልተተሮገመ ብሎ ግግም ማለት ለምኑ ይሁን??
☞ የታዘዝነው ሙተሻቢህን ወደ ሙሕከም በመመለስ ሙሕከም ከሆነው ጋር በሚስማማ መልኩ መቶርገም ነው እንጂ በተገላቢጦሾ አይደለም።
ምክኒያቱም : አሏህ ሙሕከም የሆኑት አንቀፆችን ﺃﻡ ﺍﻟﻜﺘﺎﺏ
በማለት ገለጿቸዋል። ማለትም የቁርኣን ዋና እና መመለሻ ናቸው።
"አሏህ በቁርኣን የተናገረውን ለማፅደቅ ከተባለ":
ታዲያ ለማፅደቅ ሲባል የግድ በቀጥታው መቶርገም አለበት ?!
በግልፅ በቁርኣን ላይ በፍጡራን አገላለፅ እና ከጉድለት የጠራ እንደሆነ ተቀምጦ ሳለ… ግልፅ(ሙሕከም) እና የማያሻማ አንቀፅን ችላ ብሎ ትርጉም አልባ አድርጎ የተለያዩ ትርጉሞችን የያዘ አንቀፅ ላይ የሙጥኝ ብሎ በቀጥተኛውን ትርጓሜ ለመተርጎም መሟጋት ለምን?
ይህ እውን " ልበ–እውርነት" እና በዝንባሌና በተሽቢህ መጠመድ አይደለምን?
አሏህም «እነዚያ ልባቸው የጠመሙ ሙተሻቢህ የሆኑ አንቀፆችን ይከታተላሉ» ያለን እነዚህ አይደለምን?!
የግድ እያንዳንዱ አንቀፅ በቀጥታው መቶርገም አለበት የሚል መርህስ ከዬት የመጣ ነው።?
በዚህ የተጣመመ አካሄድ የምንሄድ ከሆነ ምን ያክል አስቀያሚ የጥመት አረማመድ መሆኑን ለመረዳት:
ይህንነ አንቀፅ ልብ እንበል …
አሏህ በቁርኣን እንዲህ ይላል፦
ﻭَﻣَﺎ ﻛَﺎﻥَ ﺭَﺑُّﻚ ﻧﺴِﻴّﺎً
ትርጉም፦ «ጌታህ ራሺ አይደለም» በማለት አሏህ በግልፅ ራሱን ከመርሳት አጥራርቷል።
በሌላ አንቀፅ ደግሞ እንዲህ ይላል፦
ﻓَﺎﻟﻴَﻮْﻡَ ﻧَﻨْﺴَﺎﻫُﻢْ ﻛَﻤَﺎ ﻧَﺴُﻮﺍ ﻟِﻘَﺎﺀَ ﻳَﻮْﻣِﻬِﻢْ
ﻫَﺬَﺍ
⇨ጥንቃቄ! ( ﻧﻨﺴﺎﻫﻢ ) የሚለው በቀጥተኛው ቢተረጎም= «እንረሳቸዋለን» የሚል ትርጉም ይሰጣል… ታዲያ አሏህ ራሱን በግልፅ ያጠራበት (መርሳት) በህሪን… "በቁርኣን የመጣውን ለማፅደቅ በቀጥታው መተርጎም አለበት!" በሚል ያንን አንቀፅ ችላ በማለት አሏህ በ"መርሳት" ይገለፃል ይባላልን??
☞( ﻧﻨﺴﺎﻫﻢ )
የሚለው ትርጉም ኢብኑ ዐባስ እንዳሉት፦
«በቅጣታቸው ውስጥ እንተዋቸዋለን» ማለት ነው።
ታዲያ ቀጥተኛው ትርጉም በመውሰድ ብቻ "ማፅደቅ" ይረጋገጣል ተብሎ አንቀፁ የሚያስተላልፈውን ትርጉም ማዛባት ( ﺗﺤﺮﻳﻒ) ማድረግ ተገቢ ነውን?!
ይልቅ… ይህንን አንቀፅ በቀጥታው መተርጎም ያንን "ሙሕከም" የሆነው አንቀፅን ትርጉም አልባ ማድረግ ነው።
# ክፍል (2) « ይቀጥላል»…