ከውርስ በዝምታ ወይም ያለበቂና ህጋዊ ምክንያት የተነቀለ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ ከጠቅላላ የኑዛዜ ተጠቃሚ ጋር እኩል ወራሽ ሆኖ የሟችን የውርስ ሃብት ሊካፈል የሚገባ ስለመሆኑ፣ ሟች ካለው ሃብት እጅግ አነስተኛ የሆነ ንብረት /ሀብት/ ለተወላጁ በኑዛዜ የሰጠ እንደሆነ በውጤት ደረጃ ተወላጁ የተነቀለ መሆኑን መገንዘብ የሚቻልና ተወላጁ ከሌሎች የጠቅላላ ኑዛዜ ተጠቃሚዎች ጋር እኩል መካፈል ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 912, 938, 939, 915, 1014 እና 1123 ላይ ከተቀመጡት ድንጋጌዎች ግንዛቤ መውሰድ ይቻላል ። ቅጽ/11 ሰ/መ/ቁ/58338 t.me/ethiolawtips share #Join 1.8K viewsedited 17:05