Get Mystery Box with random crypto!

መስነፍ አያዋጣህም! በህይወትህ በጣም ወሳኙ አሁን የገጠመህ ችግር ወይ የሁኔታዎች ከባድ መሆን አ | Motivating Ethiopia👍❤

መስነፍ አያዋጣህም!

በህይወትህ በጣም ወሳኙ አሁን የገጠመህ ችግር ወይ የሁኔታዎች ከባድ መሆን አይደለም፤ ያንተ ቆራጥነት ነው! ምን ድረስ ላመንክበት ለመጓዝ ወስነሀል ነው ጥያቄው!

ረሀብ ቢሰማህ "ካገኘው እበላለው ካላገኘው ችግር የለውም" አትልም እኮ፤ ያንን ምግብ ለማግኘት በቆራጥነት ዋጋ ትከፍላለህ እንጂ አይንህ እያየ በረሀብ አትሞትም።

አሁንም አይንህ እያየ መስነፍ የለብህም፤ ማመንታት የት ሊያደርስህ? ተነስና ዋጋ ክፈል! ለራስህ ብቻ ሳይሆን ለምትወዳቸውና ለብዙዎች የምትደርስ አስፈላጊ ሰው ነህ! ዳይ ወደ ተግባር!