Get Mystery Box with random crypto!

'አይጥ ነው እያደንኩኝ ያለሁት ወይስ ጥንቸል? በህይወታችሁ ትላልቅ ነገሮች ላይ ትኩረት ለማድረግ | Motivating Ethiopia👍❤

"አይጥ ነው እያደንኩኝ ያለሁት ወይስ ጥንቸል?
በህይወታችሁ ትላልቅ ነገሮች ላይ ትኩረት ለማድረግ እንደዚህ ብላችሁ ራሳችሁን መጠየቅ አስፈለጊ ነው...


አንበሳ አይጥን የመያዝ ፣ የመግደልና የመብላት አቅም አለው ፤ ነገር ግን አይጧን ለመያዝ ከውስጡ የሚወጣውና የሚባክነው ሀይል አይጧን በልቶ ከሚያገኘው ሀይል በጣም ይበልጣል...

ስለዚህ በየቀኑ አይጥ አያደነ የሚኖር አንበሳ ቀስ በቀስ በረሃብ ምክንያት አንድ ቀን መሞቱ አይቀርም,,,አንበሳ በአይጥ ብቻ መኖር አይችልም..አንበሳ በህይወት ለመኖር ጥንቸል ታስፈልገዋለች ፤ ጥንቸል ትልቅ እንስሳ ነው ...
አንበሳ ጥንቸልን ይዞት ለመግደል ከፈለገ ፍጥነትና ጥንካሬ ያስፈልገዋል .....አንዴ ከያዘው ግን ልክ እንደድግስ ለሙሉ በተሰቦቾ ይደርሳል ምግቡ....አንበሳ በጥንቸል ስጋ ለረጅም ግዜ ደስተኛ የሆነ ኑሮ ሊኖር ይችላል..."


ስለዚህ በደንብ ለይታችሁ ማወቅ አስፈለጊ ነው


ግዜያቹን እና ሀይላቹን አይጥን ለመያዝ ነው እያባከናቹ ያላችሁት?? መልሱ አዎ ከሆነ!!፡ አይጥን አየበሉ መኖር ለአጭር ግዜ የደስታ ስሜት እንዲሰማን ሊያደርግ ይችላል..
ነገር ግን ከግዜያት በኋላ መሞታችን አይቀርም።


ስለዚህ የቀናቹ መጨረሻ ላይ " ዛሬ ቀኑን ሙሉ አይጥ ሳድን ነው የዋልኩት ወይስ ጥንቸል?" ብላችሁ ራሳችሁን መጠየቅ አስፈለጊ ነው።