Get Mystery Box with random crypto!

የናፍቆት ደብዳቤ..... የጦይባው አባቴ ፡እምነግርውህ አለኝ። አንዲት የ | Ethio iselamic gerup

የናፍቆት ደብዳቤ.....

የጦይባው አባቴ ፡እምነግርውህ አለኝ።
አንዲት የሐበሻ ወዳጅዎ `` የኔ ነቢ ምን ትመክሩኛላችሁ`` ስትላችሁ ••ስሜ ሲጠራ ተንሰፍሰፊ •• እንዳሏት ሰማሁ...
ውዴ ይሄ ከላምችሁ የብዙውን እንቅልፍ ነስቷልኮ!....ናፋቂዎ ፊዳ ይሁንሎትና ስለእርስዎ ደግሜ ላዋያችሁማ
የውስጥ ዐለሜን ነቀርሳ በእናንተው ገሽላጭ ንፋስ አገኘሁትና መዳሃኒቱን ክጀዬ ለናንተው አማከርኳችሁ....ወዳጆችዎን ከጎኔ ሰብስቤ።

ሶሃባችሁ ያለውን ሰምቼባችኋለው...ግን ለምን አባኮ? እንዴት ለኔ ለከንቱው ብለው ያንን ሙሸረፍ አካልዎ ያጎሳቁላሉ? የኔ ዐለም ሶሃባው የነገረኝኮ ••የዛህራ አባት የሚበሉት የገብስ ዳቦ ደረቅ ከመሆኑ የተነሳ ጉሮሯቸው ጋር ሲደርስ በውሃ...•• አልጨርሰውም አባኮ! እንዴት ለኔ ብለው ድፍን መዲና እማይበላውን የገብስ አይነት ከጓዳዎ ያስገባሉ? እጅዎ ምስራቅ እና ምዕራቡን ደባብሶ ካሳደገ በኋላ ደረቅ ገብስ ሲያነሱበት ጸሃይ ተጋረደችልዎት....ያንን የአሏህ ቃላት ሚስጥር የሚያንቆረቁር ውብ ከንፈርዎን ጣፋጭ ሲያርቁበት ጨረቃ ተገመሰችልዎት....እውነቱን እያወቃችሁት የምነግራችሁ ደግሞ ከጸሃይቷም ይሁን ከጨረቃ ስብራት የናፋቂዎ፡ ሐበሻ በቀይ ባህር ተጋርደው ወዲያ ማዶ ያሉት ልጆችዎ የልብ ሥብራት እንደሚብስ ነው........ድረሱልን የኔ ዐለም ካልሆነማ ሰላም የለም።

ከጣፋጩ በበላን ቁጥር የትዝታችሁ መጋዝ ደርሶ ላይ ውስጣችንን ከሚገዘግዘን ለአንዴም ቢሆን ከዚያ ለምለም ቁባ ሥር በመላኢካ ሰሪር አረፍ ብላችሁ ለእርሶ ተብሎ ከተተከለው የአዘል ዘይቱን ስትቀምሱ፡ እስከ ሰርመድ ከሚፈላላችሁ ወይን ስትጎነጩ እንያችሁ.....ወለው እንኳ በመናሜ!

ሰላም ይድረሶት ሆዴ

@aymu_hubi
@aymu_hubi
Aýmú-hùbì
#Share woduchi
#Like for more eishqe