Get Mystery Box with random crypto!

' እርዳታ የጫኑ ከ150 በላይ ተሽከርካሪዎች መቐለ ደርሰዋል ' - ስቴፋን ዱጃሪች እርዳታ የጫኑ | Freelance Jobs Ethiopia

" እርዳታ የጫኑ ከ150 በላይ ተሽከርካሪዎች መቐለ ደርሰዋል " - ስቴፋን ዱጃሪች

እርዳታ የጫኑ ከ150 በላይ የጭነት ተሽከርካሪዎች መቐለ መድረሳቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል።

የተመድ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች ትናንት በሰጡት መግለጫቸው ፥ የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ከ5 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው የትግራይ ህዝብ የሚፈልገውን መጠነ ሰፊ እርዳታ በየእለቱ እየላከ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በአካባቢው ባለ ግጭት ወደ አንድ ወር ለተጠጋ ጊዜ ወደ ትግራይ የሚያስገባው መንገድ ተዘግቶ የቆየ መሆኑን ያስታወሱት ቃል አቀባዩ ወደ በአማራ ክልልም በደሴ እና በኮምቦልቻ ለሚገኙ 100 ሺህ ተፈናቆዮች ባላፈው ሳምንት የምግብ እርዳታ መከፋፈሉን ተናግረዋል፡፡

በእነዚህ ከተሞችም እርዳታ ሲሰጥ በ1 ወር በተቃረበ ጊዜ ውስጥ የመጀመሪያው ነው ብለዋል፡፡

በሚቀጥሉት ሳምንታት የWFP እና አጋሮቹ ወደ 450 ሺ ለሚደርሱ ሰዎች የምግብ እርዳታ የሚያቀርቡ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

በአካባቢው ላይ ባለ አለመረጋጋት የተነሳ በኢትዮጵያ ሰአብአዊ ምላሽ ለመስጠት አሁንም ችግር እንደሆነ መቀለጡን ዋና ጸሀፊው አመልክተዋል፡፡

WFP በ1,700 ተሽካርካሪዎችን ሊጫን የሚችል ከ67 ሺ ሜትሪክ ቶን በላይ የሚሆን እህል በሰሜን ኢትዮጵያ ያከማቸ መሆኑን ስቴፋን ዱጃሪች አስታውቀዋል፡፡

ይህ ወደ 3 ነጥብ 7 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብን ለሁለት ወራት መመገብ የሚችል መሆኑን ገልጸው፣ ይሁን እንጂ ከፍተኛ የገንዘብና የነዳጅ እጥረት መኖሩን ማሳወቃቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

#WFP #UN

@freeActNews