Get Mystery Box with random crypto!

#ምትኬ #ደራሲ_HiLA ክፍል-21 ሂወት በድግግሞሽ የተሞላች ነገር ግን ሰርክ አዲስ የሆነ | ኢትዮጵያዊነት የኪነ-ጥበብ ሥራዎች በትረ ጊዮን ካስት ኤጀንት

#ምትኬ

#ደራሲ_HiLA

ክፍል-21

ሂወት በድግግሞሽ የተሞላች ነገር ግን ሰርክ አዲስ የሆነች የምትጣፍጥ የምታጓጓ ናት ዛሬ ያስተዋልናትን ፀሀይ ነገም ደግመን ማየት እንናፍቃለን የትላንቱን ዝናብ፣ አየር አበባ ተክል ሌላው ቢቀር የማንወደውን የጠላነውን ሰው እንኳ ነገ ማየት እንሻለን ዛሬ የሰራነውን ነገ ስንደግመው አይሰለችንም ህይወት የድግግሞሽ ውጤት ብትሆንም ሁሌ ተናፋቂና አዲስ ናት በተለይ ደግሞ የምንወዳቸው ሰዎች በዙሪያችን ሲሆኑ ሂወት ታሳሳለች እኔ አሁን ላይ ፈጣሪ በብዙ ሰዎች ባርኮኛል እናቴን የማፈቅረውን ብሩክን እህት የሆነች ጓደኛዬን ቤቲዬን ልጄ ሴናን የእማዬ አጋዝ ፈለቁን እነዚህን ሁሉ ወደሂወቴ አምጥቶ ደስተኛ አርጎኛል ታድያ ከዚህ ወዲያ እኔ ምን አነሰኝ ፈጣሪንስ ምን እጠይቃለሁ? ምን የጎደለኝ አለና ደፍሬ ጠይቀዋለሁ? አምላክን ማማረር አይሆንብኝም? እንደው ብጠይቀው አምላክ እራሱ አይታዘበኝም?
አሁን ላይ አንድና አንድ ሀሳቤ ከብሩኬ ጋር መጋባት መሞሸር እናቴን እንደምትለው አለሟን ማሳየት ነው የኔ ሀሳብ ፈጣሪ እድሜ ጤና በዙሪያዬ ያሉቱን ሀሉ ይስጥልኝ እንጂ ሌላው ሁሉ ትርፍ ነው
ይኸው ስራ ከጀመርኩ 1አመት ሞልቶኛል እኔና ብሩኬ ለወደፊት ቤታችን አንዳድ ነገሮች እያስተካከልን ነው በርግጥ የብሩኬ ቤት የተሟላ ቢሆንም ያው ከአንድ ሁለት ያውም የትዳር አጋር ሲኖር አንድ አይደለምና ብዙም ባይሆን ነገሮችን እያስተካከልን ነው ብሩኬ እማን አብራን እንድትኖር ቢፈልግም የኔ እናት ግን ፈቃደኛ አይደለችም በቃ እማ እንዲ ናት "ልጆች ከተጋቡ ትዳር ከያዙ በኋላ ከቤተሰብ መራቅ አለባቸው ምክንያቱም እንደው አይደለም ሰው እና ሰው ጥርስና ጥርስም ፣ ምላስና ጥርስም ይጋጫል እና በነፃነት ለመነጋገር አይችሉም ሁሉም ቤተሰብ ለልጁ ስለሚያደላ አንዱን ማስቀየሙ ሆድ መሻከሩ አይቀርም ስለዚህ ቃሉም ሰው እናትና አባትን ይተዋል ከሚስቱም ይጣበቃል ተብሎ ተፅፏል መራቅ አለባቸው" ብላ ታስባለች
እማዬ በዚህ ሀሳቧን ብደግፋትም ከአጠገቤ እንዳትርቅ ስለምፈልግ ብዙ ለመንኳት እሷ ግን "ይኸውልሽ ምትክ አባትሽ ጥሎኝ ወደ መኖሪያው ወደ እርስቱ ሰማይ ቤት ሲሄድ እኔ እዚች የኪራይ አለም ላይ ብቻዬን እንዳልሆን አምላክ አንቺን የአይን ማረፊያዬን ብሌኔን ሰጠኝ ደግሞ አንቺ እንደምታገቢ ቤተሰብ እንደምትመሰርቺ አምላክ ሲያስተካክል ሴናን አጫዋች የብቻዬ ልጅ አርጎ ሰጠኝ እና የኔ ልጅ አጠገብሽ ነኝ ግን ደግሞ አንድ ቤት አንኖርም ይሄ ቤትሽ ነው በፈለግሽው ሰአት መምጣት ትችያለሽ" በቃ የእማን ቃል ማስቀየር ስለሚከብድ ቤቱን በጥሩ ሁኔታ አሳደስነው ሴናዬ ልጄም ምንም እንዳይጎልባት በማሰብ ሁሉን አስተካከልን አሁን የኔም የብሩኬም ቤተሰቦች ሰርጋችንን ብቻ መጠበቅ መናፈቅ ጀምረዋል የብሩኬ እናት ሽማግሌ ለመላክ በጣም ጓጉተዋል እማዬም እንደዛው እኔ ያን ያህል የተጋነነ ሰርግ አልፈለኩም ብሩኬም በሀሳቤ አልተናደደም እናቶቻችን ግን እንኳን ሊስማሙ ጭራሽ አኮረፉን ቁጣቁጣም አላቸው የነሱ ፍላጎት ማሟላት ስለሆነ ሀሳባችን ሁሉንም ነገር በሚፈልጉት ያህል እንዲያስቡና እቅድ እንዲያወጡ መብት ከመስጠት ውጪ ምንም ማረግ አልቻልንም፡፡ የኔ ብሩክ ከመጋባታችን በፊት ስራ እንድለቅና የራሴን ቢዝነስ ሊከፍት ቢጠይቀኝም ፍቃደኛ አልሆንኩም ከተጋባን በኋላ ማስተርሴን መማር እንደምፈልግ ነግሬው ተስማምቷል "እናት በፈለግሽው መስክ የፈለግሽውን ቢዝነስ ጀምሪ እባክሽ በወር ከምጠብቂ የራስሽን ነገር ልክፈትልሽ ይህን ያህል ጊዜ ሰራሽ አይደል በቃ አሁን የሆነ ነገር ልክፈትልሽ"
"ብሩኬ ስራውን እኮ ወደዋለሁ ስራዬ ለኔ ብቻ አይደለም የሚጠቅመው እኔ ስሰራ እናቴ ደስ ትሰኛለች ትኮራለች 'ልጄ ተምራ ተመርቃ ስራ ይዛልኛለች' ትለኛለች የአባቴ ነብስ ዘወትር በኔ ደስ የምትሰኘው ስሰራ ነው ብሩኬ ቢያንስ የተማርኩበትን እንኳ መስራት አለብኝ"
"አሁንም እኮ ስራ ትተሽ ቁጭ በይ አላልኩም ግን ተቀጣሪ መሆን ይብቃሽ ነው ያልኩት"
"ገብቶኛል እኮ ፍቅር ትንሽ ጊዜ ለፍቶ ማግኘትን ሰርቶ መብላትን ልየው እናቴም ብትሆን የላቤን ሳበላት ነው ደስ የምትሰኘው ስራውም ቢሆን አድካሚ አይደለም እኮ ታቀው የለ አሁን እኮ በደንብ ለምጄዋለሁ "
"በቃ አንቺ ግትር ካልሽ እሚመልስሽ የለማ ደግሞ እኮ በምንም ማሳመን አልችልም አንቺን ወይጉድ በቃ የኔሚስት መቼም አትረቺማ "
"ሴት አይደለሁ እማዬ ሴት ልጅ ብልሀተኛ እና ባሏን በፍቅር እምታሸንፍ መሆን አለባት ትላለች ለዛ ነው"

ክፍል22 ይቀጥላል.....ከተመቻችሁ

#አስተያየት ካላችሁ...

@Babilove12

#joine #share

https://t.me/Ethioenku