Get Mystery Box with random crypto!

#ምትኬ #ደራሢ ህሊና ክፍል19 ፍቅረኛዬ አጠገብ ሳይሆን ሌላ ሰው አጠገብ የተቀመጥኩ መሰለ | ኢትዮጵያዊነት የኪነ-ጥበብ ሥራዎች በትረ ጊዮን ካስት ኤጀንት

#ምትኬ

#ደራሢ ህሊና

ክፍል19

ፍቅረኛዬ አጠገብ ሳይሆን ሌላ ሰው አጠገብ የተቀመጥኩ መሰለኝ
"እንውረድ እናት?" በቃል ሳይሆን በአንገት ምልክት ሰጠሁት ቀድሞኝ ወርዶ የመኪናውን በር ከፈተልኝ ወረጄ ክንዱን እንድይዘው እጁን አስተካከለ ተያይዘን ወደ ውስጥ ገባን አንድ ልጅ እግር አስተናጋጅ ወደ እኛ ቀርቦ በሚገርም ፈገግታ "ሰላም አቶ ብሩክ ቦታው ተዘጋጅቷል እባካችሁ ተከተሉኝ " በአግራሞት ቀና ብዬ ተመለከትኩት ፈገግ ብቻ ብሎ ልጁን ተከተልነው ወደ ሆቴሉ የመጨረሻ ክፍል በመሄድ ከቴራዙ ላይ ወጣን በነጭ ጨርቅ ያጌጡ የንጉስና የንግስት ዙፋን የሚመስሉ አንድ ጠረጴዛ እና ሁለት ወንበር ብቻ ይታያል እየመራ እንድንቀመጥ ከጋበዘን በኋላ ለመታዘዝ በተጠንቀቅ ቆመ የሚጠጣና የሚበላ ካዘዝን በኋላ አስተናጋጁ ጥሎን ወረደ ቦታው በጣም የሚማርክ እይታ አለው ወደታች ከተማውን ስመለከት አንዳች የመብራት ትርኢት የማይ መሰለኝ ሰአቱ በመምሸቱ ጭለማውን ለማሸነፍ ከየአቅጣጫው የበሩት አምፖሎች አንዳች የተለየ ስሜትን ይፈጥራሉ ያውም ከልብ ሰው ጋር ሲሆን ዝምታችንን አንዳችን መስበር እንዳለብን ቢገባንም የደፈረ አልነበረም ድንገት ዞር ስል ፈዞ እየተመለከተኝ ነበር
"ምነው ብሩኬ" አልኩት እንደማፈር ብዬ
ምነው የኔን ሴት ማየት አልችልም?" በዚህ መሀል አስተናጋጁ የታዘዘውን ይዞ መጣ ከዛም የምንፈልገውን በየፊታችን ካስቀመጠ በኋላ "መልካም ጊዜ ሰአቱ ሲደርስ አሳውቆታለሁ አቶ ብሩክ"
"እሺ አመሰግናለሁ" የምን ሰአት ይሆን እየተገረምኩ "ብሩኬ የምን ሰአት ነው?"
"አይ ተጨማሪ ነገር አዝዤ ነው.... እእእ ምን ነበር ያልሽኝ ማየት አችልም ነው?" አለ ወሬ ለማስቀየር እንደሆነ ስለገባኝ ቀየርኩለት " ኧረ ትችላለህ እንደው ሀሳብ የገባህ መስሎኝ ነው" አልኩት የመጀመሪያ ጉርሻ እየተቀበልኩት ቀጥሎ ያዝነውን ነጭ ወይን እየቀዳ ነበር
"አይ ምን ያህል እድለኛ ነኝ የሚለውን እያሰብኩ ነው በዚህ ዘመን ከነ ሙሉ ክብሯ ያለችን ሴት ማግኘት እድለኝነት ነው በዛላይ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያላት ሰው ወዳጅ ሁሉን አክባሪ ለክብሯ ሟች በቃ አንቺ እኮ ሁሉን ሳይሰስት የሰጠሽ የእጁ ስራ ነሽ እናትሽ ቢጨነቁና ከሰው አይን ቢሸሽጉሽ አይፈረድባቸውም የሚያምር ፅጌረዳን ሁሉም መቅጠፍ ይመኛል ቀጥፈዋት ስደርቅ ለመጣል ከመንከባከብ ይልቅ ለጊዜያዊ ደስታ ያጠወልጓታል አንቺንም እናትሽ እንዳጠወልጊ ስለሚሹ ነው የሚከላከሉልሽ" አውርቶ ሲጨርስ እኔም አጎረስኩት
"ብሩኬ ግን እኮ እኔ ይህን ያህል አይደለሁም በዛ ላይ ሁሉም እናቶች ለልጆቻቸው እንዲህ ነው ሚያስቡት... ግን ብሩኬ ድፍረቱን ከየት አገኘህ እማዬን የመጠየቅ?" አልኩት መብላቴን እየቀጠልኩ የጎረሰውን በወይን ካወራረደ በኋላ " በቃ ናፈቅሽኝ ናፍቆትሽ ሲያሸንፍ ልቤ ላይ አንዳች ሀይል ሰጠኝ አንቺነትሽ ከኔ ሲገዝፍ ይዘሀት ጥፋ አለኝ ለእማማ ሳላስፈቅድ ብወስድሽ ምን አልባት ገና ሳንጀምር እንጨርስና ወደ ቤት መሄድ ትፈልጊያለሽ ያለኝ ይሄ ብቻ ነበር" በመሀል ለተወሰኑ ደቂቃዎች በልባችን እያወራን ተመገብን ከዛም አስተናጋጁን በእጁ ምልክት ሰጠውና እንዲያነሳ ጠየቀው ወደኔ ጠጋጋ ብሎ ተቀመጠ አሁን በነፃነት ወይናችንን መጠጣት ጀመርን መሳሳቅ መጫወት መላፋት ደሞ መሳቅ ደሞ ማውራት ፍርሀቴ ተኖ ጠፍቶ እሱን ብቻ እያየሁ ደስተኛ ሆንኩ ብሩኬ በእጆቹ አቅፎ ክንዶቹ ላይ ጋደም አርጎኝ የፈራሁትን ጥያቄ ጠየቀኝ
" ብሌን ፈርተሻላ አብረን በማደራችን"
" አዎ ብሩኬ በጣም "
" ክብርሽን ለኔ መስጠት ትፈልጊ የለ ለምን ፈራሽ"
"ብሩኬ ሳንጋባ አይሆንም"
"አውቃለሁ እኔም እንዳፈሪ ነው ምፈልገው ሌላው ቢቀር ያመኑኝን እማማን ቃል አልበላም አፈቅርሻለሁ" ብሎ ከአገጬ ቀና አርጎ ከንፈሬን ጎረሰው ትንፋሽ እስኪያጥረኝ ሳመኝ መላ አካላቴን አንዳች ስሜት ውርር አለኝ እየሳምኩት ነው ግን እንዴት እንደሆነ አላቀም እሱ እየመራኝ ረዘም ላለ ጊዜ ሳንላቀቅ ቆየን በመሀል ድምፅ የሰማን ስለመሰለን ተላቀን ዞር ስንል ምንም አልነበረም ከጎኔ ብድግ ብሎ "መጣሁ እሺ እናት አልቆይም" ብሎ ግንባሬን ስሞኝ ተነሳ ምነው ባይነሳ እንደው እንደተቃቀፍን እንደተሳሳምን ቀናት ዘመናት በላችን ላይ ባለፋ እንደው ምናለ በተቀመጥንበት በሸበትን በጃጀን ባረጀን እንደው ጊዜው በላችን እንደ ዳመና ከበላያችን በከነፈ ብሩኬ ትንሽ ቆይቶ ተመልሶ መጣ "እናት ወደታች እንውረድ"
"ለምን ብሩኬ ቦታው ደስ ይል የለ በእናትህ እዚሁ እንሁን"
" አንድ ማሳይሽ ነገር አለ ነይ"

ክፍል 20 ይቀጥላል.....ከተመቻችሁ

#አስተያየት ካላችሁ...

@Babilove12

#joine #share

https://t.me/Ethioenku