Get Mystery Box with random crypto!

'መቼ ወንድ ልጅ ወልጄ አሳምነው ባልኩት' እያሉ የሚያልሙ በርካታ ወላጆች ናቸው።' የአማራ ፋኖ | G-NEWS

"መቼ ወንድ ልጅ ወልጄ አሳምነው ባልኩት" እያሉ የሚያልሙ በርካታ ወላጆች ናቸው።"

የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር

ሰ.አሜሪካ:- ሰኔ 18/2014 ዓ.ም
አሻራ ሚዲያ

ላስታ ላሊበላ የብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ጽጌን ሦስተኛ ሙት ዓመት መታሰቢያ በመዘከር ላይ ነች!

ጀግና ሁልጊዜም ይዘከራል፤ ሆዳም ቢረሳው ታሪክ ያስታውሰዋል። ወራሪ ቢገድለው ታሪክ እንደገና አምጦ ይወልደዋል።

ገዳዮቹ በአንድ ትውልድ ብቻ፤ እርሱንም 'ዓይንህን ለአፈር' እየተባሉ ይኖራሉ።

አሳምነው በቅብብሎሽ ወደ ፊት በሚመጡ ትውልዶች ሁሉ ይኖራል።

ከአዲስ አበባም ሆነ ከሀገር ውጭ ዘመድ ለመጠየቅ ወደ አማራ መስተዳድር የሚዘልቅ ካለ፤ ከገጠር እስከ ከተማ ብሎም ከቆላ እስከ ደጋ በተለያዩ የአማራ አካባቢዎች በርካታ ሕፃናት የሚጠሩበት አንድ ስም ገኖ ይሰማል፦አሳምነው!!!

ይህ ስም ገና ለብዙ የአማራ ሕፃናት መጠሪያ ይሆናል።

"መቼ ወንድ ልጅ ወልጄ አሳምነው ባልኩት" እያሉ የሚያልሙ በርካታ ወላጆች ናቸው።