Get Mystery Box with random crypto!

ከፍቶሽ እንዳላይ ══ ❁ ══ ዳን አድማሱ @ethiobooks | ከስነ-ፅሁፍ ዓለም

ከፍቶሽ እንዳላይ
══ ❁ ══
ዳን አድማሱ
@ethiobooks

ከፋኝ ያንቺን እንባ ከዓይንሽ ሳየው
አዝኗል ለካስ ልብሽ ደስታም የለው
እንኳን አዝነሽለት ይህን ዓለም
ስቆም የሚሞላ ከቶ አይደለም
ለሀዘን ፊት አትስጪው ጭራሽ
ሕይወት ላትኖሪያት ደግመሽ
ለኔ ደስታዬ ነው ብታዪ
ምንም ዓይኔ ከፍቶሽ ባላይ

ጊዜን ላይገዛ ሰው ላይመልሰው
ቢያዝን ቢጨነቅ ትርጉም ላይሰጠው
ያልፋል ይሄ ቀን አንቺን ያለፋው
እስከዚያው ዓይንሽ ማንባቱ ይብቃው

ቀኑም ቢጨልም ሰማዩም ቢመሽ
ጠዋት ይሆናል ይነጋል አይዞሽ
ነገን ለሚያስብ ተስፋን ላዘለ
ሲያድር ከዛሬ ሌላ ቀን አለ
[ከፍቶሽ እንዳላይ ... እንዳላይ
አዝነሽ እንዳላይ ... እንዳላይ] 2×


ከፋኝ ያንቺን እንባ ከዓይንሽ ሳየው
አዝኗል ለካስ ልብሽ ደስታም የለው
እንኳን አዝነሽለት ይህን ዓለም
ስቆም የሚሞላ ከቶ አይደለም
ለሀዘን ፊት አትስጪው ጭራሽ
ሕይወት ላትኖሪያት ደግመሽ
ለኔ ደስታዬ ነው ብታዪ
ምንም ዓይኔ ከፍቶሽ ባላይ

ፀሐይ ባትወጣ ቢያይል ደመናው
ቢከብድሽ እንኳን እሾህ ጋሬጣው
ለቀን አለቃም ቀን አለውና
አሮጌው በአዲስ ይተካል ገና

ቀኑም ቢጨልም ፀሐዩም ቢመሽ
ጠዋት ይሆናል ይነጋል አይዞሽ
ነገን ለሚያስብ ተስፋን ላዘለ
ሲያድር ከዛሬ ሌላ ቀን አለ
[ከፍቶሽ እንዳላይ ... እንዳላይ
አዝነሽ እንዳላይ ... እንዳላይ] 6×||


@ethiobooks