Get Mystery Box with random crypto!

እወድሃለሁ ══ ❁✿❁ ══ ፀደኒያ ገ/ማርቆስ @ethiobooks | ከስነ-ፅሁፍ ዓለም

እወድሃለሁ
══ ❁✿❁ ══
ፀደኒያ ገ/ማርቆስ
@ethiobooks


[ጥፋቴን አምናለሁ፣ አዎ በድያለሁ፣
እንዴትስ ደፍሬ ማረኝ እልሃለሁ፣] 2×
ጨንቆኛል እኔ ከቶ እንዴት ብዬ
ዓይንህን አያለሁ።


ቂም እንዳልያዝክብኝ ፍፁም ባምንብህም፣
እኔ አፌን ሞልቼ ማረኝ አልልህም፤
በገዛ ጥፋቴ ስሸሽህ እኖራለሁ፣
አንተን በማጣት ራሴን ቀጥቻለሁ፤
'ወድሃለሁ ..... 'ወድሃለሁ
እወድሃለሁ ..... ቃሌ ነው
'ወድሃለሁ ..... 'ወድሃለሁ
እወድሃለሁ ..... ይኸው ነው።


ጥፋቴን አምናለሁ፣ አዎ በድያለሁ፣
እንዴትስ ደፍሬ ማረኝ እልሃለሁ፣
ጨንቆኛል እኔ ከቶ እንዴት ብዬ
ዓይንህን አያለሁ።


የበደልኩህ በደል እንቅልፌን ነስቶኛል፣
ሰላሜን አጣሁ እንዴት ይሻለኛል፤
ጥፋቴን አልክድም አስቀይሜሃለሁ፣
ብቻ ተረዳልኝ ዛሬም እወድሃለሁ።
'ወድሃለሁ ..... 'ወድሃለሁ
እወድሃለሁ ..... ቃሌ ነው
'ወድሃለሁ ..... 'ወድሃለሁ
እወድሃለሁ ..... ይኸው ነው።

እ ወ ድ ሃ ለ ሁ።||


@ethiobooks