Get Mystery Box with random crypto!

ከ ህዳር 14 እስከ ታህሳስ 12 ለተወለዱ በሙሉ »» ዞዳይካቹ ወይም ኮኮባቹ ሳጁታሪያስ ይባላል | ኢትዮ ASTROLOGY

ከ ህዳር 14 እስከ ታህሳስ 12 ለተወለዱ በሙሉ

»» ዞዳይካቹ ወይም ኮኮባቹ ሳጁታሪያስ ይባላል
»» ሳጁታሪየስ አመሰገንኩ ሲል ይሳደባል አሞገስኩ ሲል ያዋርዳል አስደሰትኩ ሲል ያሳዝናል እርሱ ግን ያጠፋውን ነገር አይታየውም ፣ በነሱ ቤት ለሰው አሪፍ ነገር ማረጋቸው ነው፣ ምን ክፉ ቃል ወጣኝ ብሎ ይገረማል፣ ጥፋቱ ቶሎ አይገባውም።

»» የሳጁታሪየስ ተፈጥሮ ከመሰሪነት እና ከተንኮል ሙሉ ለሙሉ የፀዳ ነው። ብዙዋቹ ፈጣን፣ ችኩልና ደንባራ ናቸው ፣ ነገር ስራቸው ሁሉ ሞቅና ደብለቅ ያለ ሆኖ ለዛና እርጋታ ግን ሊጎለው ይችላል።

»» ሳጁታሪየስ ሲናገር እጆቹን የማወናጨፍ ልማድ አለው።

»» ሁሌም ይደናፈቃሉ፣ ተደናፍቆም በወደቀ ጊዜ ያንጠለጠለው ወይም ያዘለው ሻንጣ ይወድቃል፣ ወድቆም ይበረገዳል።

»» የሳጁታሪየስ አይኖች እንደ ክዋክብት የሚያበሩና በደስታ የሚቁለጨለጩ ናቸው፣ የሰከነ ተፍጠሮ የላቸውም ፣ ይቁነጠነጣሉ ፣ ከአንድ ስፍራ ዘለግ ላለ ጊዜ አይቀመጡም፣ የሌላ ዞዳይክ የጎላ ተፅኖ ከሌለባቸው በስተቀር።

»» ለእንስሳት ልዩ ፍቅር አላቸው በተለይ ደግሞ ለፈረስ እና ለውሻ

»» ንግግራቸው ፍርጥ ያለ ነው። ብዙ ግዜ መድረክን ያፈቅሩታል

»» ወንዶቹም ሆኑ ሴቶቹ በልጅነታቸው ወደ ሀይማኖት ይሳባሉ፣ በእድሜ ከፍ ካሉ ጊዜ ግን የሃይማኖትን ቀኖና ጥያቄ ውስጥ ማስገባት ይጀምራሉ።

»» ሳጁታሪየሶች ሁሌም ተጓዦች ናቸው ፣ ውርርድ እና ቁማር ይወዳሉ እድለኞችም ናቸው ።
»» የማስታዎስ ችሎታቸው ድንቅ የሚባል ነው፣ በነፃነት ለመኖር የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፣ በጠባብ ክፍል፣ በትንሽ ገንዘብ፣ በአነስተኛ እውቀት ሲገደቡ ይጨንቃችዋል።

»» እድገት እንጂ ውድቀት አይታያቸውም፣ ሁሉም ነገር ይቻላል ብለው ነው ሚያስቡት።

»» የወደፊቱንም ነገር የመተንበይ ልዩ ችሎታ አላቸው ።

Share Share

@ethiokokeb @ethiokokeb
@ethiokokeb @ethiokokeb