Get Mystery Box with random crypto!

ኮከቦችና ወሲባዊ ግፊት ከ12 እስከ 1; በቅደም ተከተል አሊስ ሞራሌ የተባለች የአስትሮኖሚ ባለሙ | ኢትዮ ASTROLOGY

ኮከቦችና ወሲባዊ ግፊት ከ12 እስከ 1; በቅደም ተከተል

አሊስ ሞራሌ የተባለች የአስትሮኖሚ ባለሙያ የወሲባዊ ፍላጎትና መነቃቃት መነሻ በማድረግ 12ቱን ኮከቦች በደረጃ አስቀምጣለች። በጽሁፏም ከዋክብት ሊቢዶ የተሰኘው ሆርሞን ላይ ተጽዕኖን እንደሚያሳድሩ አስቀምጣለች።

በዚሁ ጽሁፏ ሁሉም ኮከቦች (የሰው ልጆች) ለወሲብን ፍላጎትና ግፊት እንደሚኖራቸው አስቀምጣ አንዳንዶች ለወሲብ ያላቸው መነሳሳትና ግፊት (sex driven) ከፍ ያለ ሲሆን የአንዳንድ ኮከቦች መነቃቃት ደግሞ ሌሎች መሠረታዊ ፍላጎቶታቻቸው ሲሟሉ እንደሚመነጭ አስቀምጣለች።

እንግዲህ ለደረጃ አሰጣጡም መሰረታዊ መነሻ ይህ መሆኑ ነው። እኛም እንግዲህ በርሷ ትንተና ተመስርተን ከመጨረሻው በመጀመር እንቃኛለን።

12ኛ ሊብራ

ለሊብራዎች በዚህ ደረጃ መቀመጥ ወሲብን ከመጥላታቸው የመነጨ አይደለም። ምክንያቱ የተለያየ መልክ ያለው ጥልቅ ግንኙነትን ከመሻታቸው እንጂ። እንደ ጓደኛ፣ ቤተሰብ ወዘተ. ለሊብራዎች ወሲብ ተግባራዊነት የሚኖረው ፍቅርንና ቃል መግባትን ተከትሎ ነው። ከዚህ አንጻር ሁልጊዜም ወይም በድንገት ወሲብ የመፈጸም ሁኔታቸው ከሌሎች ኮከቦች በተነጻጻሪ ዝቅ ያለ ነው።

11ኛ አኳሪየስ

የአኳሪየሶች የበዛው ፍላጎት ነጻነት ነው። ከዚህ አንጻር ወሲባዊ መስተጋብራቸው በጥቂቱ እንኳን ከዚህ በተቃራኒ የሚቆም መስሎ ከተሰማቸው ምርጫቸው ፊታቸውን ማዞር ነው። ይህ መለያው አየር የሆነ ኮከብ (አኳሪየሶች) ለወሲብ ብቻ ሲሆን ጭንቅላታቸውን በደመና ውስጥ የሚቀብሩ አይነት ሲሆን የግንኙነቱም መሠረት ወሲባዊ መስተጋብር ብቻ ከሆነ ለመጨበጥ የሚከብዱ አይነት ናቸው።

10ኛ ቪርጎ

በርግጥ ቪርጎዎች በመኝታ ላይ ደፋሮች (adventuries) ናቸው። ራሳቸውን ለቀቅ አድርገው የሚገልጡበትም ቦታ ነው። ችግሩ እነርሱን ወደዚያ ከማድረስ ላይ ነው። ቪርጎዎች አዕምሯቸውን ነጻ የሚያደርግላቸውና ውስጣቸውን እንደፈለጉ እንዲገልጡ የሚያደርጋቸው ወዳጅ ቀዳሚው ጥያቄና መሠረት ነው።

በቀደመው ክፍል አስትሮሎጂስቷ አሊስ ሞራሌ ሁሉም ኮከቦች (የሰው ልጆች) ለወሲብን ፍላጎትና ግፊት እንደሚኖራቸው አስቀምጣ ኮከቦች ግን ሊቢዶ በተሰኘውን ወሲባዊ መነቃቃትን የሚወስን ተፈጥሮ ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩበት መግለጿን አስቀምጠን ነበር።

በዚህ መነሻት አንዳንዶች ለወሲብ ያላቸው መነሳሳትና ግፊት (sex driven) ከፍ ያለ ሲሆን የአንዳንድ ኮከቦች መነቃቃት ደግሞ ሌሎች መሠረታዊ ፍላጎቶታቻቸው ሲሟሉ እንደሚመነጭ ማስቀመጧን ጠቅሰን ከዚህ አንጻር ከ 12-10 ያለውን ደረጃ የያዙ ኮከቦች አስቀምጠን ነበር ያበቃነው። የዛሬው ተከታይ እነሆ!

9ኛ ጀሚኒ

ጀሚኒዎች ፈጥነው የወሲባዊ መጋጋል ውስጥ የማይገቡ ናቸው። ንግግር፣ ሳቅና ጨዋታ እና የአዕምሮ መጣጣም ስሜታቸው እንዲነቃቃ አስፈላጊ ናቸው። በሂደቱ የሚፈጠር ትንሽ ስህተት ስሜታቸውን ሊያቀዘቅዘው ይችላል።

8ኛ ካፕሪኮርን

ካፕሪኮርኖች ከረር ያሉና ወግ አጥባቂ መሆናቸው አንዱ መታወቂያቸው ነው። በርግጥ ይህ ሁኔታቸው በመኝታ ክፍል ሲሆን ቀነስ ብሎ ይስተዋላል። ነገር ካፕሪኮርኖች ከወሲባዊ ግንኙነት በላይ ራሳቸውን በስራ መወጠርና መቅበር ደስተኛ ሆነው እንዲቆዩ የሚያደርጋቸው ነው።

7ኛ ካንሰር

ካንሰሮች የፍቅር/ወሲብ አጋራቸው ትርጉም የሚሰጡትና የሚንከባከባቸው እንዲሆን ይሻሉ። ከወሲብ እውነተኛውን ደስታ ለማግኘት መተማመን (trust) መሠረታዊው ጉዳይ እንደሆነ ያስባሉ። ይህ ደግሞ ጊዜ ሊወስድ ቢችልም ካንሰሮች ለመጠበቅ ያላቸው ትዕግስት ከፍላጎት በላይ ነው።

6ኛ ፓይሲስ

ፓይሲሶች በርግጥ በወሲብ ይዝናናሉ፤ ፍላጎታቸውም ጥሩ ነው። ነገር ግን የስሜት ግንኙነትና ቅርበት ከወዳጃቸው ጋር እንዲኖር ይሻሉ። ይህን ካገኙ የፍላጎታቸው ገደብ አበላያቸው ያለው የቤቱ ጣሪያ ይሆናል። ይህ ቅርርብ ከሌለ ደግሞ ስሜታቸው በአንታርክቲካ እንደሚገኝ በረዶ ይሆናል።

5ኛ ሊዮ

የሊዮዎች የወሲብ መነቃቃትና ፍላጎት በፍቅር/ወሲብ አጋራቸው ላይ የተመሠረተ ይሆናል። እንደሚያስቡት የጫካው ንጉስ አድርገው የሚቀበሏቸውና ታላቅነታቸውን ያለማወላወል የሚመሰክሩ ሲሆኑ ሊቢዶ የተሰኘውና የወሲብ መነቃቃት ደረጃን የሚወስነው ሆርሞን እንደ እሳት መንቀልቀል ይጀምራል። ያን መሠል የስሜት ግንኙነት ከሌለ ደግሞ ፑፍ...ስሜታቸው ከምትገምቱት ፍጥነት በላይ ስሜታቸው ይቀዘቅዛል።

4ኛ ሳጁታሪየስ

ሳጁታሪየሶች በአየር የሚወከሉ እንደመሆናቸው ፍላጎታቸው መልከ ብዙ ነው። ከሌሎች ኮከቦች በላቀ በመኝታ ክፍል ያልተለመዱ ነገሮችን የሚከውኑ ናቸው። ቃል መግባትና ቁርጠኝነትም አንዳንድ ጊዜ ሊስተዋልባቸው የሚችል ነው። በህይውታቸው የተለያየ ነገርን እንደመፈለጋቸው ጊዜያዊ የወሲብ ግንኙነትን መፍቀድ በጠረጴዛው ከተቀመጡ አማራጭች ውጪ ላያደርጉ የሚችሉበት እድል ሰፊ ነው።

3ኛ ኤሪስ

የኤሪሶች ገዢ ፕላኔት ማርስ ናት። ማርስ ተጽዕኖ ከምታሳድርባቸው ጉዳዮች አንዱ ደግሞ ወሲብን ነው። ከዚህ አንጻር ሂሳቡን እናንተ አስሉት። 1+1=2 ማለት አይቸግራችሁምና። ኤሪሶች ማማመለልኑም ሆነ በወሲብ አጋራቸውን መሪ ሆነው መጋራቱን እኩል ሊባል በሚችል ደረጃ የሚዝናኑበት ነው። Almost!

2ኛ ታውረስ

ስሜትን መረዳትና ማጣጣም የሚችሉበት ታውረሶች ሁሉንም አይነት ሊባል በሚችል ደረጃ አካላዊ መነካካቱንና ደስታን ማግኘቱን ይወዱታል። ከዚህ አንጻር ከዝርዝሩ ቀዳሚዎቹ ተርታ መሠለፋቸው የሚገርም አይሆንም። ይህንን ካሳኩም በኋላ ቀሪ ስራዎቻቸውን በተሻለ ደረጃ የመፈጸም አቅማቸው ከፍ የሚል ነው፤ ጥሩ ስሜትም ይኖራቸዋል።

1ኛ ስኮርፒዮ

መቼም እስከ ዘጠኝ ያሉትን ደረጃዎች የሳተ ቢኖር እንኳን በዝርዝሩ ቀዳሚ የሚሆነውን መሳት የሚቻለው አይመስለኝም። አዎ! ስኮርፒዮ ነው! ግምታችሁ ትክክል ነው ። ስኮርፒዮዎች ከፍ ባለ የወሲብ ፍላጎታቸው ይታወቃሉ። ይህም በቅርበትና በመሞከር ፍላጎታቸው የሚወረስ ነው።

ብዙ የወሲብ አጋሮችን የሚፈልጉ ሆነው ግን አይደለም፤ እንዲያውም ምርጫቸው የተጠና ነው። (they are selective) ምክንያቱ ደግሞ ድብቅ ባህሪዎቻቸውን እንዲያውቁ የሚፈቅዱላቸው ሰዎች ጥቂት ከመሆናቸው የመነጨ ነው።


ምንጭ ኮኮቦች ስለ እኛ

Share Share

@ethiokokeb @ethiokokeb
@ethiokokeb @ethiokokeb