Get Mystery Box with random crypto!

ከጥር 13 እስከ የካቲት 12 ለተወለዳቹ በሙሉ። »» ዞዳይካቹ ወይም ኮኮባቹ አኳሪየስ ይባላል | ኢትዮ ASTROLOGY

ከጥር 13 እስከ የካቲት 12 ለተወለዳቹ በሙሉ።

»» ዞዳይካቹ ወይም ኮኮባቹ አኳሪየስ ይባላል

»» አኳሪየስ ኮኮብ ያለው ሰው እውቀትን በማንበብ፣ በመመርመር፣ በመስማት አንድአንዴም ከየት እንደሚያውቀው ለመገመት በሚያስቸግር መልኩ የሰበሰበውን እውቀትና ጥበብ ወደ ሰው ልጆች ይረጫል።

»» የአኳሪየስ ኮኮብ ያለው ሰው ዕውቀቱን ሲዘራ በሰው ልጆች መካከል ልዪነት አያደረግም፣ በአርሶ አደሮች ጉባዬ ላይ ስለ አስትሮፊዚክስና ስለ ማይክሮባዮሎጂ ሊናገር ይችላል፣ በገዳም ለተሰበሰቡ መነኮሳት ስለ ዳርዊን የዝግመተ ለውጥ ትወራ ማብራርያ ሲሰጥ አያስገርምም።

»» አኳሪየስ ስለመጭው ዘመን አስቀድሞ ያያል፣ የአዲስ ዘመንን ንጋት ያበስራል፣ ከጊዜው ቀድሞ የሚፈጠርና ኑሮውንም በመጭው ዘመን ውስጥ የሚየደርግ ፍጡር ነው፣ በዚህም ምክንያት በሌሎች ዘንድ እንደ ተራ ሊታይ ይችላል።

»» አኳሪያሶች ያልተጠበቀ ነገርን ሁሌም ያደርጋሉ፣ አካሄዳቸውን መገመት ያስቸግራል፣ የብዙሃኑን አመለካከትና እምነትን ፉርሽ ማድረግን ይደሰቱበታል፣ በልተጠበቀ ድርጊታቸውና ንግግራቸውም ወግ አጥባቂ ሰዎችን ማስደንገጥ ይወዳሉ።

»» አለባበሳቸው ወቅቱን ይጠብቅ አይጠብቅ ልብ አይሉትም፣ ሲፈልጋቸው በባዶ እግራቸው ከአደባባይ ይወጣሉ፣ የሳቀባቸውን መልሰው ይስቁበታል፣ ነገረ ስራቸው ሌላው ሰው ከሚያስብውና ከሚያደርገው የተገላቢጦሽ ነው።

»» በሌላ በኩል ደግና ቸር ናቸው፣ የተቸገረን በመርዳት አቻ የላቸውም፣ የበጎ አድራጎት ድርጅትን በገንዘብ ይደግፋሉ፣ ስለብዙሃኑ ይጨነቃሉ፣ የህዝብን ኑሮ የሚያቀሉ ፈጠራዎችንና ሐሳቦችን ያመነጫሉ

»» ሌላው መገለጫቸው ደግሞ ጓደኛ ፣ ወዳጅ ወይም ባልንጀረ የሚለው ቃል ነው ፣ ጓደኝነትን ከብዙ ነገር በላይ አክብረውት ይታያሉ፣ የቅርብና የነፍስ ጓደኛ የሚሉት ባይኖራቸውም የሰውን ልጅ በሞላ እንደ ጓደኛቸው ያዩታል፣ አለማቀፋዊ ጓደኝነትን እና ወንድማማችነትንም አጥበቀው ይሰብካሉ፣ ጓደኛ የሚለውን ቃል ደጋግመው ስለሚጠቀሙም በዚ ይታወቃሉ።

»» አኳሪየስ የለየለት መርማሪ ነው ፣ ሰውን መኪናን፣ ራዲዮን ዕፅዋትን ሁሉን ይመረምራል፣ ይፈትሻል አንዱን ሲጨርስ ወደ ሌለው ይሄዳል ፣ ቀጣዩም ተመርማሪ እርሶ ሊሆኑ ይችላሉ፣ አምዕሮ በብዙ ኪሎሜትሮች መጥቆ እና ጠልቆ የሚሄድ ነው ፣ በስውር ማይክሮስኮፕ ሰዎችን አየቆራረጠ የሚመረምር ነው ሚመስለው፣ ምንም እስከማይቀረው ድረስ ብትንትን አድርጎ ያቆታል፣ እርሱ ግን አይታወቅም፣ ትንግርት ነው፣ ምርመራውን ሲጨርስ ጥሎት ይሄዳል፣ የዚህ ሁሉ ሰበብ ጉጉ መሆኑ ነው።

»» አይኖቻቸው ሩቅ ተመልካች ነው፣ የሚያልሙና ትንግርትን ያዘሉ ነው ሚመስሉት ፣ ታድያ የአኳሪያስ አቀራረብ ቀዝቀዝ ያለ ነው፣ እርጋታውም ያስገርማል፣ ለኑሮ ያዎቅበታል የነገን ቢያልምም የዛሬን በወጉ ይኖራል፣ ገንዘቡን በጥንቃቄ ይይዛል።

»» የአኳሪየስ ቁመና ልዕልናን የተጎናፀፈ ነው ፣ ገፅታቸው እንደ ሳንቲም ላይ ምስል ቁርጥ ያለና ጠርዝ አለው፣ ሲናገሩ ጭንቅላተቸውን ወደታች ወይም ወደ ጎን ዘንበል የማድረግ ልማድ አለቸው፣ ለብቻቸውም ፈገግ እያሉ ሊሆን ይችላል።

»» ለራሱ የሆነ ግዜ ሁሌም ያስፈልገዋል፣ ብቸኝነቱንም ይናፍቃዋል

»» ከሌሎች ኮኮቦች የበለጠ አእምሮ ጥልቅ እና ምጡቅ ነው ከእርሶ ጋ እያወራ ከጎን ሚደረገውን ከነ ሁኔታው ይራዳል።

»» አኳሪየሶች የወግ፣ የልማድና የባህል ፀር ናቸው። እንዲሁም ልዩ የመነጠል አባዜ አለባቸው ፣ ሰዎችም በአግባቡ አይረዱትም፣ የነሱ ኑሮ በነገ እና በተነገ ወዲያ ነው ፣ ዘሬን ብቅ የሚለው አልፎ አልፎ ነው ፣ስለዚህም ለተራው ሰው ግራ ፍጥረት ሆኖ ይታያል፣ እሱም ይህን ያይና መነጠሉን ያበዛዋል፣ እኛ ተራዎቹ ደግሞ ምን እያደረገ ነው ብለን እንገረማለን።

አስትሮሎጂ " አኳሪየስ ዛሬ የሚያስበውን ቀሪው አለም ከ50 አመት በኅላ ያስበዋል " ይለናል።
»» አኳሪየሶች የጂኒየስነት ምልክት ነቸው፣ ከስመጥር ሰዎች 70% የሚሆኑት እነሱ ናቸው።

»» የአእምሮ መረበሽ ለደረሰባቸው አዘኔታን ያሳያሉ፣ ትከሻቸውም ይነገራችዋል፣ እነሱን በማናገር ብቻ ያረጋጉታል፣ ለራሳቸው ግን የማይረጋጉበት ጊዜ ይበዛል።

»» አመለካከታቸው ሰፊ ነው ፣ ፍርድ ገምድልነት የለባቸውም፣ ሁሉም ሰው ወይ እህቱ ወይ ደግሞ ወንድሙ ነው፣ በነዳያንና በሀብታሞች መንደር ይዞራሉ።

»» ብቸኝነቱን አይገዳደሩበት ፣ ብቻውን መሆን ይፈልጋል፣ አንድአንዴ ቁዘማ ውስጥ ይጠፋል ብዙ ግን አይቆይም ወዲያዎ ይወጣል።

»» ቁርጥ ባለ ጌዜና ተግባር ውስጥ መታሰርን ይፈራሉ ሆኖም አንዴ ልበቸውን ከገኟቸው በተባለው ቦታ ይገኛሉ፣ አንዴ ከመኖት አመኖት ነው ማንም ምንም ቢል ይሰማ ይሆናል እንጂ አያምንም፣ እስኪያምኖት ግን ግዜ ይፈልጋል።

»» የአኳሪየሶች ፍልስፍና ሁሉም እንደፍጥርጥሩ ይኑር ነው፣ ግለሰባዊነት በሱ ዘንድ መከበር አለበት።

»» አኳሪየሶች በቂ እንቅልፍና ንፁ አየር ማግኘት አለባቸው።
»» ልቦናው በጣም ስሱ ነው ፣ የውሸት እና የማጭበርበር ቀንደኛ ጠላቶችም ናቸው።

»» አኳሪየሶች በሚያስቡት ነገር ውስጥ የነገ ፍንጭ አለበት፣ ወዳልታሰበው አለም ተጉዘው ትንግርታዊ ምስጢሮችን ይቀስማሉ፣ ይህም ኢንቲዪሽን እና ሳይኪክነትን ያላብሳችዋል፣ለምሳሌ አብርሃም ሊንከን ስለሞቱ ከነአስገራሚ ዝርዝሩ አስቀድሞ አውቆ እንደነበር በታሪክ ተመዝግቧል።

»» አኳሪየስ ማበደርንም ሆነ መበደርን አይወድም፣ በስጦታ መልክ ደጋግሞ ሊሰጥህ ይችላል በድር ግን አጠይቀው፣ ወይ ደግሞ ቶሎ መልስ።

»» ከ12 ዞዳየኮች በውበትና ቁንጅና ተቀዳሚ ናቸው ሚባሉት ቶረሶች፣ ጄሚኒዎች፣ ሊብራዎችና አኳሪየሶች ናቸው፣ ከአራቱ አንደኞቹ የትኞቹ ናቸው በሚለው ላይ የአስትሮሎጂ ሊቃውንት አንድ አይነት አቋም ይዘው ባይታዩም ፣ በዛ ያሉት ግን አኳሪየሶችን ያስቀድማሉ።

»» ሳጁታሪየሶች መጪውን ጊዜ በህልም እና በራእይ መያት ይቻላቸዋል፣ አኳሪየሶች ግን መጪውን ጊዜ በእውኑ ያቁታል፣ እዚያው ነበሩ፣ ከዚያ መተው ነው የሚነግሩን፣ እንደ ነብይ ናቸው ፣ ነብይ ደግሞ ባገሩና በዘመኑ አይከበርም ይሰደዳል፣ እንዲሁም ይሰየፋል፣ ህብረተሰቡ አኳሪየሶችን ራሱ ያጠፋችዋል ራሱ ደግሞ ቆይቶ ይዘምርላችዋል።

በ1473 እስከ 1543 የኖረው ፓላንዳዊው ኒኮላስ ኮፐርኒካስ መሬት እና ሌሎች ፕላኔቶች ፀሃይን ይዞራሉ ስላል ብቻ በድንጋይ ተቀጥቅጦ ተገደለ፣ እሱ ከሞተ ከብዙ አመት ቧላ ግን መሬት እና ሌሎች ፕላኔቶች አለምን እንደሚዞሩ አለም የሚያቀው እውነት ሆነ።

Share Share

@ethiokokeb @ethiokokeb
@ethiokokeb @ethiokokeb