Get Mystery Box with random crypto!

#DebreTaborUniversity ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምሀርት መስኮች ያስተማራ | ኢትዮ ዩኒቨርስቲ መረጃ

#DebreTaborUniversity

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምሀርት መስኮች ያስተማራቸውን 1 ሺህ 238 ተማሪዎች ቅዳሜ ሐምሌ 09/2014 ዓ.ም ያስመርቃል።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ እና በኤክስቴንሽን መርሃ ግብር በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 163ቱ የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ዳዊት ብርሀኑ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ 9ኛ ዙር ሰልጣኞቹን የሚያስመርቅ ሲሆን 369ኙ ሴት ተማሪዎች ናቸው።
━━━━━━━━━━━━━━━━━
Join &
|||_Support us
@ethio_university_info
@ethio_university_info