Get Mystery Box with random crypto!

#Reminder የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ላመጣችሁ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን የማስተካከያ ጊዜ ዛሬ | Ethio University 🎓

#Reminder

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ላመጣችሁ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን የማስተካከያ ጊዜ ዛሬ የካቲት 02/2015 ዓ.ም ያበቃል።

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጣችሁና በመንግስት ተቋማት ገብታችሁ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እንድታስተካክሉ በትምህርት ሚኒስቴር የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ዛሬ ያበቃል።

በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የምትሹ ተማሪዎች ማመልከቻችሁን እና ደጋፊ ሰነዶቻችሁን በቀጣዩ ሊንክ ብቻ መላክ አትዘንጉ
https://student.ethernet.edu.et

@ETHIO_UNIVERSITY1