Get Mystery Box with random crypto!

' እንዳትጭበረበሩ ተጠንቀቁ ' የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ህብረተሰቡ #እንዳይጭበረበር ራሱን | Ethio techs Link

" እንዳትጭበረበሩ ተጠንቀቁ "

የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ህብረተሰቡ #እንዳይጭበረበር ራሱን እንዲጠብቅ አሳሰበ።

ከአገልግሎቱ ዛሬ መግለጫ ደርሶናል።

የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት በላከው መግለጫ ፤ " የጤናማ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች ለአገር ከፍተኛ እና የማይታካ አዎንታዊ ፋይዳ እንዳላቸው ማንም የሚገነዘበው ነው " ብሏል።

ሆኖም አንዳንድ ግለሰቦች እና ድርጅቶች " በኢንቨስትመንት እና በአብረን እንስራ ስም ተጨባጭና የተሟላ መረጃ ሳይሰጡ ከፍተኛ ገንዘብ ከህብረተሰቡ እየሰበሰቡ መሆናቸውን " መረጃ ደርሶኛል ብሏል።

ገንዘብ ከህብረተሰቡ ለመሰብሰብም እጅግ አትራፊ የሆነ የግብርና እና የሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ላይ መሰማራታቸውን በመግለፅ ቅንጡ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን በዝቅተኛ ዋጋ መግዛት እንዲሁም አክሲዮን በመግዛት በአጭር ጊዜ ውስጥ ትርፋቸውን በእጥፍ ማሳደግ እንደሚችሉ በተለያዩ መንገዶች እያስተዋወቁና ገንዘብ እየሰበሰቡ መሆናቸው ተገንዝብያለሁ ብሏል።

ጤናማ የፋይናንስ እንቅስቃሴ እና ኢንቨስትመንት በእጅጉ የሚደገፍ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በኢንቨስትመንት ስም የሚፈፀሙና ሊፈፀሙ የሚችሉ ወንጀሎችን መከላከል በዚያው ልክ አስፈላጊ ይሆናል ብሏል አገልግሎቱ።

ህብረተሰቡ ከመሰል ድርጊቶች ጋር ተያይዞ ሊፈፀም ከሚችል መጭበርበር ራሱን እንዲጠብቅ፣ የጥንቃቄ እርምጃም እንዲወስድ አገልግሎቱ አሳስቧል።

የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ፤ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ፣ ሽብርተኝነትንና ጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎችን ብዜት በገንዘብ የመደገፍ ወንጀሎችን መከላከልና መቆጣጠር እንዲቻል ከተለያዩ አካላት የፋይናንስ ወንጀል ነክ መረጃዎች በመቀበል፣ በመሰብሰብና በመተንተን ውጤቱን ለሚመለከታቸው አካላት በማሰራጨት እንዲሁም በመሰል ጉዳዮች ላይ ከህግ አስከባሪ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

ህብረተሰቡ ከወንጀሎቹ ጋር በተያያዘ በአንድ በኩል ራሱን ከወንጀል በመጠበቅ አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ ደግሞ  ለተቋሙ ጥቆማ በመስጠት የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎትን በምን በኩል ላግኛቸው ? ስልክ +251118128261 ፤ ኤሜል info@fis.gov.et

@tikvahethiopia