Get Mystery Box with random crypto!

#እንድታውቁት ከሚያዚያ 16 ጀምሮ በመላው አዲስ አበባ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅነት በ ' ቴሌብ | Ethio techs Link

#እንድታውቁት

ከሚያዚያ 16 ጀምሮ በመላው አዲስ አበባ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅነት በ " ቴሌብር " ብቻ ተግባራዊ ይደረጋል ሲል የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል።

በ " ቴሌብር " ነዳጅ ስለ መቅዳት አሸከርካሪዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ ነጥቦች ምንድናቸው ?

☞ በቅድሚያ የ " ቴሌብር "ተጠቃሚ መሆን፤
☞ በቂ ክፍያ የቴሌብር አካውንት ውስጥ መኖሩን ማረጋገጥ፤
☞ የ " ቴሌብር " የሚስጥር ቁጥርዎን ማስታወስና በአግባቡ መያዝ፤

የአከፋፈል ሁኔታው ምን ይመስላል ?

‣ የነዳጅ ማደያ ሰራተኞች የተጠቃሚውን ስልክ ቁጥርና የሚከፍሉትን የገንዘብ መጠን ሞልተው ሲጨርሱ የእርስዎ ስልክ ላይ የሚስጥር ቁጥርዎን እንዲያሥገቡ የሚጠይቅ አጭር መልዕክት ይመጣሎታል፤

‣ በመቀጠል የሚስጥር ቁጥርዎን ከማስገባትዎ በፊት ከደረስዎት መልዕክት ላይ የተቀመጠ ገንዘብ መጠን ትክክል መሆኑን ያረጋግጡ፤ ካረጋገጡ በኃላ የሚስጥር ቁጥርዎን ያስገቡ፤

‣ በመጨረሻም ክፍያው ከተፈፀመ በኃላ የክፍያውን ማረጋገጫ አጭር የመልዕክት ቁጥር ወዲያውኑ ይደርሶታል።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ፤ የተሽከርካሪ ነዳጅ ግብይት ከሚያዚያ 16/2015 ዓ.ም ጀምሮ በ " ቴሌ ብር " ብቻ የሚፈፀም በመሆኑ ሁሉም አሽከርካሪ እንዳይጉላላ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ
tikvahethiopia

                   #Share
@ethio_techs @ethio_techs