Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ የምነግራችሁ Maths እና Physics እንዴት መነበብ እንዳለባቸው ነው፡፡ ተከተሉኝ ፦ | Top students

ዛሬ የምነግራችሁ Maths እና Physics እንዴት መነበብ እንዳለባቸው ነው፡፡ ተከተሉኝ ፦


በመጀመሪያ Maths ፣Physicsን ለማጥናት ራሳችንን በስነልቦና ማዘጋጀት አለብን ፣ማለትም ከባድ አለመሆናቸውን ራሳችንን ማሳመን አለብን ፡፤በመቀጠልም ትምህርቶቹን ስናጠና እነዚህን ማረግ አለብን ፦


ለPhysics

concept መያዝ ያስፈልጋል ፡፡ እንዲሁም formula በመሸምደድ ፋንታ proof ማድረግ በጣም ጠቃሚ ናቸው ፡፡ እንዲሁም ዋና ዋና የሚታወቁ የ physics ህጎችን ለምሳሌ ፦
፡-Newtons law of motion.
፦ Pascal principle
፦ Archemedian principle ወዘተ...ህጎችን መያዝ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡

ለMaths

ስናጠና ደግሞ የtopicኡን ህግ እንዲሁም ጥያቄዎቹ የሚሠሩበትን መንገድ step by step በደንብ ለመረዳት መሞከር እንዲሁም ያልገባን ጥያቄ ካለ የተለያዩ አጋዥ መፅሀፍችን( ከላይብረሪ ብትጠቀሙ ብዬ እመክራለሁ ) እና ት/ቱን የሚያስተምረውን አስተማሪ መጠየቅ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡


ብዙዎች የሚሳሳቱት ነገር

ደግሞ Maths ፣Physics ማጥናት ያለብን ፈተና ሲደርስ ብቻ አይደለም፡፡ሁልጊዜ ቢያንስ በዚያን ቀን የተማርነውን topic መከለስ አለብን እንዲሁም ቢያንስ በዚያን ቀን ከተማርነው topic 5 ጥያቄ ብንሠራ በጣም ይጠቅመናል ፤ ምክንያቱም እነዚህ ት/ቶች እንደሌሎች የሽምደዳ ት/ቶች ለፈተና concept እንዲሁም formula ሸምድደን በመግባት ብቻ የምንሰራቸው ከመሰለን በጣም ተሳስተናል፣ ይልቁንስ topicኡን በመረዳት እና የተለያዩ ጥያቄዎችን በመለማመድ የምንሠራቸው የት/ት አይነቶች ናቸው፡፡ አሁን ተግባባን አይደል


ከእነዚህ ት/ቶች ደስ የሚለው ነገር ደግሞ topicኡን አንዴ በደንብ ከተረዳነው ከጭንቅላታችን አይጠፉም ስለዚህም ፈተና ሲደርስ በመጨናነቅ ፈንታ ራሳችንን በተለያዩ ጥያቄዎች challenge የማድረግ እድሉን እናገኛለን


Share
Share


https://t.me/high_preparatory
https://t.me/high_preparatory