Get Mystery Box with random crypto!

Hydraulics and water supply Lecture . ለዛሬ ደሞ የ ላየኛው የምድር ውሃ | Ethio Engineers

Hydraulics and water supply Lecture
.
ለዛሬ ደሞ የ ላየኛው የምድር ውሃ (surface water) ለማጣራት የምንጠቀማቸው ዘዴዎች ኣዘጋጅተናል
.
⓵ስክሪኒንግ (screening) - ይህ የመጀመረርያው የማጣራት
ደረጃ ሲሆን በዚህ የማጣራት ዘዴ ውስጥ በውሃው ላይ የሚንሳፈፉ ግዙፍ አካላትን ለምሳሌ የዛፍ ጉቶ ፣ግንድ፣ ቅጠል እና ልዩ ልዩ የፕላስቲክ ተንሳፋፊ ቁሳቁሶች ወደ ዋናው የማጣሪያ ገንዳ እና ስርዓት
እንዳይገቡ ያግዳል ።
.
⓶ማርጋት (Coagulation )፦ በዚህ የማጣራት ደረጃ ላይ
ለአይን እይታ ያነሱ ጥቃቅን
አካላትን (Particle size 10^-7cm የሚሆኑ) በማርጋት እና
የኬሚካል ቻርጃቸውን ኒውትራላይዝ የሚያረግ ኬሚካል በመጨመር እርስ በእርሳቸው
እንዲሳሳቡ ማድረግ ነው ።
ለዚህ የአልሙኒየም ፖሊመሮች (Alum) እና አይረን (Fe+3)
አገልግሎት ላይ ይውላሉ።
እንደ የቁልቋል ተክል ያሉ የተፈጥሮ አርጊዎች (coagulants) መጠቀምም ይቻላል
.
⓷ጉግለት (Flocculation)፦ ይህ እርከን ፤ ማርጋት
(coagulation ) ወቅት የረጉ ጥቃቅን አካላትን እርስ በእርሳቸው ቦንድ እስኪፈጥሩ እና እርስ በእርሳቸው ተጣብቀው እስኪጓግሉ ውሃው በተለያየ ፍጥነት የሚማሰልበት ነው።
ይህ ዘዴ ሜካኒካል ወይም ማኑዋል በሆነ መልኩ ይተገበራል።
.
⓸መዝቀጥ/ማዝቀጥ (sedimentation) ፦ በፍሎኩሌሽን ወቅት የጓጎለው ጥቃቅን አካላት በዚህን የማጣራት ደረጃ እንዲዘቅጡ ይደረጋል ። ይህ ዘዴ የሚተገበረው የሚጣራው የውሃን ፍጥነት በመቀነስ ግራቪቲን ተጠቅሞ እንዲዘቅጥ ማድረግ ነው።
በግራቪቲ ለማዝቀጥ የሚከብዱ እጅግ ጥቃቅን ቆሻሻዎችን በፍሎኩሌሽን ወቅት ስንጠቀማቸው የነበሩ ኬሚካሎችን በመጠቀም እንዲዘቅጡ ይደረጋል።
.
⓹ ማጥራት (filtration ) ፦ በዚህ የማጥራት ደረጃ ከማዝቀጥ
ደረጃ ያለፉ ጥቃቅን ቆሻሻዎችን እጅግ ጥቃቅን ቀዳዳዎች ባሉት አካል (medium ) እንዲያልፍ በማድረግ የድፍረስነቱን መጠን እጅግ መቀነስ ነው።
.
⓺ማከም (Disinfection) ፦ ከላይ በተጠቀሱ የማጣሪያ ሂደቶች የተጣራው ውሃ
(በዋነኛነት ከተለያዩ ህይወት ከሌላቸው ጥቃቅን ቆሻሻዎች)
ለህብረተሰቡ ለአገልግሎት
ከመድረሱ በፊት በዚህ ሂደት (ዲስኢንፌክሽን) ማለፍ አለበት ።
ምክንያቱም ውሃው ለአገልግሎት የሚቀርበው ከተለያዩ በአይን ከማይታዩ በሽታ አምጪ ተህዋስያን ነፃ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው ። ዲስኢንፌክሽን ውሃውን በማፍላት ፣ ሚካኒካል
በሆነ መልኩ ፣ ለጨረር በማጋለጥ (radiation ) እንደሁም በኬሚካል ሊከናወን ይችላል።
በሃገራችን በዋነኛነት
ሃሎጅኖችን (ብሮሚን ክሎሪን እና አይኦዲን ) በመጠቀም
ኬሚካል በመጠቀም ውሃን እናክማለን ።

ከዚህ ሁሉ የማጣራት ሂደት በኋላ የተጣራው ውሃ ይጠራቀምና
ለተጠቃሚዎች ይዳረሳል።
.
ስለ surface waterን የማጣራት ሂደቶች ጥቂት የሆነ ገለፃን እንዳደረግንላችሁ ተስፋ
እናደርጋለን ። ርእሱ ሰፊ እንደመሆኑ ዳግመኛ በጥልቀት ለመዳሰስ ቃል እንገባለን
ም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።