Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ መረጃ ሰበር ዜና Addis Mereja

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_addis_mereja — አዲስ መረጃ ሰበር ዜና Addis Mereja
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_addis_mereja — አዲስ መረጃ ሰበር ዜና Addis Mereja
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_addis_mereja
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 385
የሰርጥ መግለጫ

| ETHIOPIA
ፈጣን ፣ ተአማኒ የሆኑ ብቻ ሰበር ዜናዎች ከሀገርቤትም ከ ውጭም ይቀርቡበታል፡፡
● ከውጭ
● ከሀገር ውስጥ
● ሰበር ዜናዎች
● ተአማኒ ዜናዎች
● አዲስ መረጃዎች ያገኛሉ ፡፡
NEWS & MEDIA CHANNEL

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-06 14:22:36
ፓርላማው ዛሬ ባካሄደው 6ኛው ልዩ ስብሰባ በወቅታዊ የፀጥታ እና በንጹሐን ዜጎች ጉዳይ ላይ ተወያይቶ የውሳኔ ሐሳብ አሳለፈ

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛው ልዩ ስብሰባ፤ በወቅታዊ የፀጥታ እና በንጹሐን ዜጎች ጉዳይ ላይ ተወያይቶ የውሳኔ ሐሳብ አስተላለፈ።

የዕለቱን መርኃ-ግብር በግፍ ለተጨፈጨፉት ዜጎች የአንድ ደቂቃ የኅሊና ጸሎት በማድረግ የጀመረው ምክር ቤት፤ የሚከተሉትን የውሳኔ ሐሳቦች አስተላልፏል፡፡

በዜጎች ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ እጅግ የኮነነው ምክር ቤቱ፤ በአገራችን በየትኛውም ክልልና አካባቢ በሲቪል ዜጎች ላይ የሞትና የአካል ጉዳት ያስከተሉ እና ንብረት ያወደሙ ግለሰቦች በሕግ እንዲጠየቁ እንዲደረግ ሲል ውሳኔ አሳልፏል። በየደረጃው ያለው አመራር አካል፣ የጸጥታ አካል እና የፍትሕ ተቋም የህዝቡን ደህንነትና ሠላም በጥብቅ እንዲያስከብር፣ አጥፊዎች ለሕግ ተጠያቂነት እንዲቀርቡ እንዲደረግ ወስኗል።


http://T.me/ethio_addis_mereja
328 viewsedited  11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 14:22:36
"ጭፍጨፋውን እየመሩት ያሉት የኦሮሚያ ክልል አመራሮች ናቸው።" - አቶ ሃንጋሳ አህመድ ኢብራሂም የህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት አባል ከተናገሩት የተወሰደ

አቶ ሀንጋሳ ዛሬ ሁለት ሰዓት በፈጀውና ከ15 ሺህ በላይ ተመልካቾች በተከታተሉት የፌስቡክ የቀጥታ ስርጭት በኦሮምኛ (የተወሰኑ ቁልፍ ነገሮችን ደግሞ በአማርኛ) አስተላልፈዋል፡፡ በዚህም፣

አማራን ኦሮሚያ ውስጥ የመግደል እና የመጨፍጨፍ እቅድ የኦነግ ሳይሆን የኦሮሚያ ብልጽግና እቅድና ተግባር ነው፣ አብዲ ኢሌ ሲነሳ ሶማሊያ ሰላም እንደሆነው ሁሉ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ በክልሉ ያሉ ባለስልጣናትን እስር ቤት በማስገባት ሰላም ይስፈን፣ ዶ/ር አብይ ከለማ የቀረበ ወዳጅ አልነበረህም በሱ ላይ የጨከንክ በሽመልስ ላይ መጨከን እንዴት አቃተህ ብሏል።

- እነ ሽመልስ ዙሪያውን ከበው ሊበሉህ ነው፣ ሊጨርሱህ ነው የመጨረሻው ሰዓት ላይ ደርሰሃል አይንህን ግለጥ! አማራን ኦሮሚያ ውስጥ መጨፍጨፍ የሚጎዳው ከአማራ ይልቅ ኦሮሞን ነው፣ መቼ ነው ዶ/ር አብይ ከአትክልት ስራ ወጥተህ ጠንከር ያለ ስራ የምትሰራው፤ መቼ ነው የከበበህ መከራ የሚታይህ፣ መቼ ነው ሊበላህ የተነሳው ጅብ የሚታይህ ብሏል።

- ዛሬ አማራን እየገደለ የሚመጣው ሀይል መቆሚያው አንተ ቤት (አራት ኪሎ) ነው ፣ ሽመልስ እና ፍቃዱ ታደሰን ወደ እስር ቤት ካላስገባህ ከዚህ ጥቃት ጀርባ አንተ አለህ ማለት ነው፣ ለአብዲ ኢሌ ክፍት የሆነ እስር ቤት ለሽመልስ እና ፍቃዱ ዝግ የሆነው ኦሮሞ ስለሆኑ ነው ወይስ አዛዡ አንተ ስለሆንክ ነው ብሏል።

http://T.me/ethio_addis_mereja
314 viewsedited  11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 02:25:28
ዛሬ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ላይ የደረሰው ድብደባ ተገቢ አይደለም

ዛሬ 200 ገደማ የሚሆኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በኦሮሚያ የተፈጸመውን ግድያ ለማውገዝ አደባባይ በወጡበት የፌዴራል ፖሊስ አባላት የፈፀሙት ድብደባ ብዙዎችን ያስቆጣ ነበር!

በሰልፉ ላይ "ሞት በቃ" እንዲሁም "አማራ እየሞተ የምትበለጽግ ኢትዮጵያ የለችም" የሚሉ መፈክሮች ታይተዋል።

የፌዴራል ፖሊሶች ተማሪዎቹ ለተቃውሞ እንደሚወጡ ቀድሞ መረጃ ስለደረሳቸው ብዙ ተማሪዎች ከዋናው ግቢ እንዳይወጡ " አፈና" አድርገዋል ሲሉ የግቢው ተማሪዎች ተናግረዋል።

ተማሪዎቹ "ምንም አይነት ሰልፍ የሚያስከለክል ነገር ሳይዙ "ተቃውሞ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። አስተጋብተናል ካሏቸው መፈክሮች መካከል " ሞት በቃን፣ አማራ እየሞተ የምትበለጽግ ኢትዮጵያ የለችም፣ ዘር ተለይቶ መገደል ይብቃ፣ እኛ እንደማንኛውም ብሔር ብሔረሰቦች እኩል መታየትና እኩል ተከብሮ መኖር እንፈልጋለን" የሚሉት እንደሚገኙበት ገልፀዋል። 

የተቃውሞ ድምጽ የሚያሰሙት ተማሪዎች አምስት ኪሎ የሚባለው አካባቢ ሲደርሱ ግን ፖሊሶች ድብደባ እንደፈፀሙ እና ብዙ የተጎዳ ተማሪ መኖሩንም ገልፀዋል።

አንደኛው ተማሪ "በድብደባው ብዙ የተጎዳ ሰው አለ። አሁን የካቲት 12 ሆስፒታል የሚገኙ ሦስት ወይም አራት ተማሪዎች አሉ፣ በጣም ደም ፈሷቸዋል፣ ታሽገዋል፣ ሌላ እግሩን ወይም እጁን ያልተመታ የለም" ብሏል። ሰላማዊ ሰልፉም በፖሊሶች መበተኑን ተናግሯል።

ዛሬ ዋናው የአዲስ አበባ የኒቨርሲቲ በር ላይም ብዛት ያላቸው የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላትም ታይተዋል። በቦታው የነበሩ ወታደሮች ሙሉ ትጥቅ የታጠቁና ስናይፐር የሚባለውን የጦር መሳሪያ ወድረው የያዙ ነበሩ።

ሀሳብን የመግለፅ መብት ይከበር!! #በቃ

T.me/ethio_addis_mereja
698 viewsedited  23:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 14:49:40
#Update

በትናንትናው እለት በደሴ ከተማ በደረሰው የእሳት አደጋ የእሳት ማጥፊያ መኪናዎች ዘግይተዉ በመድረሳቸዉ ከፍተኛ ዉድመት ደርሷል ተብሏል

በደሴ ከተማ የእሳት አደጋ ማጥፊያ መኪና እጥረት አለ ሲሉ ነዋሪዎች ቅሬታቸዉን አቀርበዋል

በትናንትናዉ እለት በደሴ ከተማ በተለምዶዉ ስሙ ስጋ ተራ በተሰኘው አካባቢ ከምሽቱ 12 ሰዓት በአንድ የንግድ ማዕከል ላይ የእሳት አደጋ ተከስቷል። በአደጋዉ የሰዉ ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም በንብረት ላይ ዉድመት አድርሷል።

አደጋዉን ለመቆጣጠር የአካባቢዉ ወጣቶች እና ማህበረሰብ ትልቅ ሚና እንደነበራቸዉ በደሴ ከተማ በአንደኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ የሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ክፍል ሀላፊ የሆኑት ረዳት ኢ/ር ክብረት እሸቴ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።

ሆኖም የአካባቢዉ ማህበረሰብ የእሳት አደጋ መኪናዎች አደጋዉ በተከሰተበት ወቅት በፍጥነት ባለመድረሳቸው ከፍተኛ ዉድመት እንዳስከተለ ይገልጻሉ። ይህንንም ቅሬታ ትክክል መሆኑን ረዳት ኢ/ሩ ለብስራት አረጋግጠዋል።

የአካባቢዉ ማህበረሰብ ባደረገዉ ርብርብ እሳቱ ወደሌሎች የንግድ ማዕከላት እንዳይዛመት ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳደረገ ፖሊስ ያነሳል።

የአደጋዉ መንስኤ እና ያደረሰዉ ዉድመት በፖሊስ በመጣራት ላይ መሆኑንም በደሴ ከተማ በአንደኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ የሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ክፍል ሀላፊ የሆኑት ረዳት ኢ/ር ክብረት እሸቴ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።

http://T.me/ethio_Addis_mereja
622 viewsedited  11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 12:57:19
የጎንደር ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በዛሬው እለት ሰልፍ ወጥተዋል።

ብዛት ያላቸው የዩንቨርስቲው ተማሪዎች በዛሬው እለት በወለጋ ለተጨፈጨፉ ዜጎች ድምፅ ሆነዋል። ተማሪዎቹ በማንነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እና ግድያን በግልፅ መቃወማቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

http://T.me/ethio_Addis_mereja
496 viewsedited  09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ