Get Mystery Box with random crypto!

የአትክልትና ፍራፍሬ እና የፍጆታ እቃዎች ሥርጭት ባለፉት ስምንት ወራት ኮርፖሬሽኑ በ2015 በጀት | Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)

የአትክልትና ፍራፍሬ እና የፍጆታ እቃዎች ሥርጭት ባለፉት ስምንት ወራት

ኮርፖሬሽኑ በ2015 በጀት ዓመት ስምንት ወራት ውስጥ በአጠቃላይ 110 ሺህ ኩንታል የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት ለህብረተሰቡ አቅርቧል፡፡ ከተሰራጩት ምርቶች መካከል ፍራፍሬ 37,275 ኩንታል፣ አትክልት 1,707 ኩንታል፣ የፋብሪካ ምርት 967 ኩንታል እና ስኳር 24,358 ኩንታል ይገኙበታል፡፡

ፍራፍሬ በአማካኝ ዋጋ ከነጻ ገበያው ከ40-50%፣ አትክልት በአማካኝ ዋጋ ከነጻ ገበያው ከ10-20% እንዲሁም የፋብሪካ ምርት (ቲማቲም ድልህ 850 ግራምና 1000 ግራም ብርቱኳን ማርማላት) በአማካኝ ዋጋ ከነጻ ገበያው ከ15-20% ቅናሽ በማድረግ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡

በስምንት ወሩ ውስጥ 24,358 ኩንታል ስኳር ከንግድ ቢሮ ትስስር ለተፈጠረላቸው አገልግሎት ሰጪዎችና ተቋማት (ሆስፒታሎች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ማረሚያ ቤቶች) እንዲሁም ባለኮኮብ ሆቴሎች መንግስት ባስቀመጠው ዋጋ ማሰራጨት ተችሏል፡፡

በተመሳሳይ በስምንት ወራት ውስጥ 141 ሺህ ኩንታል የፍጆታ እቃዎች ለገበያ ቀርበዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ ሸቀጦች 29,509 ኩንታል፣ የታሸጉ ምግቦች 8,575 ኩንታል፣ የቤት ንፅህና መጠበቂያዎች 8,392 ኩንታል፣ የግል ንፅህና መጠበቂያዎች 5,409 ኩንታል እና ስኳር 27,500 ኩንታል በዋነኛነት ይጠቀሳሉ፡፡