Get Mystery Box with random crypto!

የሀገር ውስጥ የፍጆታ ምርቶች ሽያጭ አፈፃፀም ባለፉት ስድስት ወራት በሀገር ውስጥ ገበያ ኮርፖሬሽ | Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)

የሀገር ውስጥ የፍጆታ ምርቶች ሽያጭ አፈፃፀም

ባለፉት ስድስት ወራት በሀገር ውስጥ ገበያ ኮርፖሬሽኑ ብር 4,101,217,587 ዋጋ ያለው 1,281,411 ሚሊዮን ኩንታል ምርትና እና የአገልግሎት ሽያጭ ለህብረተሰቡ ለማቅረብ አቅዶ ብር 3,273,864,897 ቢሊዮን ዋጋ ያለው 999,481 ኩንታል ምርት እና የአገልግሎት ስርጭት በማከናወን የዕቅዱን በመጠን 78 በመቶ በዋጋ ደግሞ 80 በመቶ አከናውኗል፡፡ የአቅርቦትና ስርጭት አፈፃፀም ከ2014 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 5 በመቶ ብልጫ አለው፡፡
በሀገር ውስጥ የፍጆታ ምርቶች ግብይት ሽያጭ ኮርፖሬሽኑ ያገኘው ገቢ ብር 5,822,656,134 ሲሆን ይህም በገቢ ድርሻ ሲታይ፡-
እህልና ቡና 65.42%፣
የምግብ ዘይት 16.29%፣
ስኳር 2.8%
የኮንስትራክሽን ግብአቶች 7.2%፣
የአትክልትና ፍራፍሬ ስርጭት 2.5 በመቶ በድምሩ 94.1% ድርሻ ሲኖራቸው ቀሪው 5.9% የሌሎች ፋብሪካ ምርቶችና አገልግሎት ሽያጭ ገቢ ድርሻ ነው፡፡

የውጭ ሀገር ሽያጭ አፈፃፀም

ኮርፖሬሽኑ በ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ላይ በውጭ ገበያ /ኤክስፖርት/ 10,290 ኩንታል እህልና ቡና በብር 80,185,520 ለመሸጥ አቅዶ 6,577 ኩንታል የተለያዩ የብርዕ፣ ጥራጥሬ፣ የቅባት እህሎች፣ ቡና እና ፍራፍሬ በብር 77,460,788 በመሸጥ የዕቅዱን በመጠን 64 በመቶ በዋጋ ደግሞ 97 በመቶ አከናውኗል፡፡
በግማሽ ዓመቱ ኤክስፖርት ከተደረገው ምርት ሽያጭ 1,484,418.70 የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡