Get Mystery Box with random crypto!

በለውጥ ስራዎች ትግበራ ዙሪያ የአካል ምልከታ ተካሄደ በኮርፖሬሽኑ የለውጥ ስራዎች (ቢ ኤስ ሲ፣ ካ | Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)

በለውጥ ስራዎች ትግበራ ዙሪያ የአካል ምልከታ ተካሄደ
በኮርፖሬሽኑ የለውጥ ስራዎች (ቢ ኤስ ሲ፣ ካይዘን፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ፣ የመመሪያዎች አተገባበር እና መሰል ተያያዥ ጉዳዮች) አተገባበር ዙሪያ የአካል ምልከታ (ሱፐርቪዥን) በማካሄድ ከሚመለከታቸው የዘርፍ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡ በውይይቱም በቀጣይ ይበልጥ የተጠናከረ የለውጥ ስራዎች ትግበራ ለማድረግ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ የአካል ምልከታው ኣላማ ኮርፖሬሽኑ ከካይዘን ልህቀት ማእከል ጋር አስቀድሞ ባደረገው የካይዘን ትግበራ ስምምነት መሰረት ችግር ፈቺ የትግበራ አካሄድን ለመተግበር እንዲያስችል ነው፡፡
በአካል ምልከታው የኮርፖሬት የህግ፣ ማህበራዊ ጉዳይና አሰራር ማሻሻያ ም/ዋ/ሥ/ አስፈጻሚ አቶ ይርጋሸዋ ተሸመ፣ የኮርፖሬት የአሰራር ዘዴና የአገልግሎት ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ትእዛዙ ኃ/ ጊዮርጊስ እንዲሁም የካይዘን ልህቀት ማእከል የስራ ኃላፊና የካይዘን አማካሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
የኮርፖሬሽኑ የቡና ማእከል፣ የእህል ማከማቻና ማደራጃ ማእከል፣ የፍጆታ እቃዎች ንግድ ስራ ዘርፍ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ ስራ ዘርፍ እና የሎጀስቲክስና ቴክኒክ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ምልከታው የተካሄደባቸው ዘርፎች ናቸው፡፡