Get Mystery Box with random crypto!

ለምርት ጥራት፣ ክምችትና ክብካቤ ባለሙዎች ሥልጠና ተሰጠ ምርትን ከተባይ ለመከላከል እንዲያስችል | Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)

ለምርት ጥራት፣ ክምችትና ክብካቤ ባለሙዎች ሥልጠና ተሰጠ

ምርትን ከተባይ ለመከላከል እንዲያስችል በእህል እጥነት (fumigation) ዙሪያ ህዳር 6 ቀን 2015 ዓ/ም ሥልጠና ተሰጠ፡፡ ሥልጠናውን ያዘጋጀው በኮርፖሬሽኑ የሰው ኃብት ልማትና ሥራ አፈጻጸም አመራር ቡድን ሲሆን ስልጠናውን የሰጠው ደግሞ ኬምቴክስ ኃ/የተ/የግል ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱ የተባይ ማጥፊያ ኬሚካል አቅራቢ ነው፡፡

በሥልጠናው የመጋዘን ተባዮችና አያያዝን ጨምሮ ሌሎች ርእሰ ጉዳዮች የተካተቱ ሲሆን ከሁሉም ክልል ግብይት ማዕከላት፣ ከኮርፖሬሽኑ የሎጀስቲክስና ቴክኒክ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት እና ከዋናው መ/ቤት የተውጣጡ የእህልና ቡና የምርት ጥራት ክምችትና ክብካቤ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡ የሥልጠናው ዓላማ የእህል ክምችትን የመንከባከብ ሥራን በአግባቡ ለማከናወን እንዲቻል እንዲሁም ምርት ሳይባክንና ሳይጎዳ ጥራቱን እንደጠበቀ ለማቆየት እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ ሰልጣኞች የተለያዩ ሀሳብና አስተያየት የሰጡ ሲሆን ለእህል ጥራት ሥራቸው አጋዥ ሥልጠና ሆኖ እንዳገኙት ገልጸዋል፡፡ ሥልጠናውን ሲያስተባብሩ የነበሩት አቶ ጌታቸው ይመር የሰው ኃብት ልማትና ሥራ አፈጻጸም አመራር ቡድን መሪ ባስተላለፉት መልእክት ሠልጣኞች ያገኙትን ዕውቀት ተግባር ላይ እንዲያውሉና ከስራቸው ያሉ ባለሙያዎችን እንዲያበቁ አደራ ብለዋል፡፡