Get Mystery Box with random crypto!

የሀሰት ሰነድ በመጠቀም የማጭበርበር ወንጀል በፈጸሙ ሠራተኞች ላይ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈ በእህልና | Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)

የሀሰት ሰነድ በመጠቀም የማጭበርበር ወንጀል በፈጸሙ ሠራተኞች ላይ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈ

በእህልና ቡና ንግድ ሥራ ዘርፍ የደብረማርቆስ ግብይት ማዕከል ኃላፊና ሠራተኞች በሀሰት የተዘጋጀ ሰነድን ህጋዊ ማስረጃ በማስመሰል ህጋዊ ላልሆኑ ሸማች ማህበራት መጠኑ 236.62 ኩንታል በቆሎ በመሸጥ ለግል ጥቅማቸው በማዋላቸው በማስረጃ በመረጋገጡ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈባቸው፡፡

የኮርፖሬት የህግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት አስፈላጊውን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች በማደራጀት ለምዕራብ ጎጃም ፖሊስ የሙስና ወንጀል ምርመራ መምሪያ አቅርቧል፡፡ የሙስና ወንጀል ምርመራ መምሪያውም በቀረበለት ማስረጃዎች መሠረት አስፈላጊውን የምርመራ ሥራ አጠናቆ ግለሰቦቹ በህግ እንዲጠየቁ ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ዓቃቢ ሕግ አቅርቧል፡፡

ጉዳያቸው በፍርድ ቤቱ ሲታይ ቆይቶ ነሐሴ 4 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት 1ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ የውብዳር ታከለ እና 2ኛ ተከሳሽ አቶ ጎራው ደሳለኝ እያንዳንዳቸው በ4 ዓመት እስራትና በአንድ ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ሲቀጡ፤ 3ኛ ተከሳሽ አቶ መስፍን ንጋቱ በ3 ዓመት ከ7 ወር እስራትና በአንድ ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጣ ፍርድ ቤቱ ወስኗል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ በተከሰሱበት የፍትሐብሔር መዝገብም በአማ/ብ/ክ/መ/ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የደብረማርቆስ ተዘዋዋሪ ችሎት ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች በክሱ መሠረት በጋራ ብር 688,632 ለኮርፖሬሽኑ እንዲከፍሉ መወሰኑን የኮርፖሬት ሥነምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት የላከልን ዘገባ ያመለክታል፡፡