Get Mystery Box with random crypto!

ለዘርፉ ሽያጭና መጋዘን ሠራተኞች በሙያ ሥነምግባር፣በሙያ ደህንነትና በምርት እንክብካቤ ዙሪያ ስልጠ | Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)

ለዘርፉ ሽያጭና መጋዘን ሠራተኞች በሙያ ሥነምግባር፣በሙያ ደህንነትና በምርት እንክብካቤ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

ለአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ ሥራ ዘርፍ ሽያጭና መጋዘን ሠራተኞች በሙያዊ የሥነምግባር፣በሙስና ወንጀል ህጎች፣በሠራተኞች ደህንነትና ጤና አጠባበቅ እንዲሁም በምርት አያያዝና እንክብካቤ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡

በስልጠናው መድረክ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዘርፉ ሥራ አስፈጻሚ አቶ መህዲ አስፋው ሲሆኑ ለሰልጣኞቹ ባስተላለፉት መልዕክት፣ለደንበኞች የሚሰጡ አገልግሎቶች ሙያዊ ሥነምግባርን በተላበሰ መንገድ መከናወን እንዳለባቸው በተለይ በድርጅቱ የተሰጣቸው የሥራ ኃላፊነት እና ንብረት በታማኝነት፤ በቅንነትና በአገልጋይነት ስሜት መወጣት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡

የዘርፉ ሥራ አስፈጻሚ አክለውም በደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ውስጥ የሚታዩ ህገ ወጥ አሠራሮች ካለፉት ዓመታት አንጻር ሲታዩ የመቀነስ አዝማሚያ ቢያሳዩም ሙያዊ ሥነምግባር በተላበሰ መንገድ ለደንበኞች አገልግሎት አለመስጠት፤ሚዛን ማጉደል፤የመንግስት የሥራ ሰዓት ማባከን፣የምርት ብልሽት በሚፈለገው ደረጃ አለመቀነስና የሥራ ተነሳሽነት ደካማ መሆን አሳሳቢ እየሆኑ የመጡ ችግሮች መሆናቸውን የቅርብ የክትትልና ቁጥጥር ሪፖርቶች (Supervision Report) ያመለክታሉ በማለት ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም የሥራ ዘርፉ በ2015 በጀት ዓመት ያስቀመጣቸውን ዋና የትኩረት አቅጣጫ የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻል፣ሀብትና ንብረትን በቁጠባ መጠቀም፤የምርት ብልሽትና ብክነትን መቀነስ፣ የሠራተኞችን ምርታማነት ማሳደግና ትርፋማ የመሆን ግቡን ለማሳካት የአቅም ግንባታ መድረኮች አጠናክሮ እንደሚሰራ አቶ መህዲ አስፋው ገልጸዋል፡፡

የዘርፉ 95 ሽያጭና የመጋዘን ሠራተኞች ለሶስት ተከታታይ ቀናት የተሰጠውን የሙያዊ ሥነምግባር፤የሙስና የወንጀል ህጎች፣የሙያ ደህንነትንና የምርት እንክብካቤ ስልጠና በትኩረት ተከታትለው አጠናቀዋል፡፡