Get Mystery Box with random crypto!

ኮርፖሬሽኑ 326 ሚሊየን 272 ሺህ 12 ብር ትርፍ ከታክስ በፊት አስመዘገበ የኢትዮጵያ ንግድ ስ | Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)

ኮርፖሬሽኑ 326 ሚሊየን 272 ሺህ 12 ብር ትርፍ ከታክስ በፊት አስመዘገበ

የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን በ2014 በጀት ዓመት 326 ሚሊየን 272 ሺህ 12 ብር ትርፍ ከታክስ በፊት እንዳስመዘገበ ተገለጸ፡፡ አመራሩና ሰራተኛው ባሳዩት ከፍተኛ አፈጻጸም ትርፋማ መሆን እንደተቻለና የተመዘገበው ትርፍ ካለፉት ዓመታት የበለጠ መሆኑን የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አቻ ደምሴ ገልጸዋል፡፡ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አያይዘውም በተገኘው አመርቂ ውጤት ለኮርፖሬሽኑ አመራርና ሰራተኞች የሶስት ወራት ደመዎዝ ጉርሻ እና የሶስት እርከን ደመወዝ ጭማሪ በማትጊያነት እንዲሰጥ በስራ አመራር ቦርዱ መወሰኑን አረጋግጠው ለኮርፖሬሽኑ ሰራተኞች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ የ2015 በጀት ዓመት የእቅድ ትውውቅ ቀጣይ መድረክ መስከረም 12/ 2014 ዓ.ም አካሂዷል፡፡ በዚህ መድረክ የ2014 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት፣ በ2014 በጀት ዓመት በኮርፖሬሽኑ እቅድ አፈጻጸም የነበሩ ክፍተቶች እንዲሁም የሰራተኛ ማህበር ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡ ከሰኣት በኋላ በነበረው መርኃ ግብር የ2015 በጀት ዓመት እቅድ ቀርቦ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡