Get Mystery Box with random crypto!

የ2015 በጀት ዓመት የእቅድ ትውውቅ መድረክ ተካሄደ የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን የ201 | Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)

የ2015 በጀት ዓመት የእቅድ ትውውቅ መድረክ ተካሄደ

የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን የ2015 በጀት ዓመት የእቅድ ትውውቅ መድረክ ከአራቱም ዘርፎች የተውጣጡ ሥራ አስፈጻሚዎች፣ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት መስከረም 9/ 2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሆቴል ቁ.2 ተካሄደ፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አቻ ደምሴ በመድረኩ መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልእክት መድረኩ ትልቅ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን በመጥቀስ የዓመቱን እቅድ በውጤታማነት ለማከናወን የሚያስችል አቅም ለመፍጠር መድረኩ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡ ከሰራተኞችም ጠቃሚ ግብአት እንደሚጠበቅም አያይዘው ጠቁመዋል፡፡ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አክለውም ኮርፖሬሽኑ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ትርፋማ በመሆኑ ለአጠቃላይ ሰራተኞች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ በየደረጃው ያሉ ሰራተኞችና አመራሮች ያደረጉት ጥረት ኮርፖሬሽኑን ትርፋማ እንዳደረገ ጠቁመዋል፡፡

በመድረኩ የኮርፖሬሽኑ የ2014 በጀት ዓመት ሪፖርት፣ በ2014 በጀት ዓመት በኮርፖሬሽኑ እቅድ አፈጻጸም የነበሩ ክፍተቶች እንዲሁም የሰራተኛ ማህበር ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡ ከሰኣት በኋላ በነበረው መርኃ ግብር የ2015 በጀት ዓመት እቅድ ቀርቦ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ በዋና መ/ቤትና በዘርፍ ደረጃ ከጀማሪ እስከ መካከለኛ ደረጃ ያሉ 400 ሰራተኞች በመድረኩ የተሳተፉ ሲሆን ከጥቂት ቀናት በኋላም ሌሎች 400 ሰራተኞችን ያካተተ ተመሳሳይ መድረክ እንደሚኖር ከወጣው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል፡፡ በቀጣይም የውይይት መድረኩ በሁሉም የክልል ግብይት ማዕከላት ተካሂዶ የማጠቃለያ መድረክ እንደሚኖር ተመላክቷል፡፡

የውይይት መድረኩን መጠናቀቅ ተከትሎ የመድረኩን ተሳታፊዎች በሙሉ ያካተተ የእራት ግብዣ ሥነ-ስርዓት ተካሂዷል፡፡