Get Mystery Box with random crypto!

ኮርፖሬሽኑን ለተቀላቀሉ አዲስ ሰራተኞች የትውውቅ ስልጠና ተሰጠ የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽ | Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)

ኮርፖሬሽኑን ለተቀላቀሉ አዲስ ሰራተኞች የትውውቅ ስልጠና ተሰጠ

የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽንን በቅርቡ ለተቀላቀሉ አዲስ ሰራተኞች የትውውቅ (ኢንዳክሽን) ስልጠና ጳጉሜ 03/ 2014 ዓ.ም ተካሄደ፡፡ ስልጠናውን ያዘጋጀው የኮርፖሬት የሰው ሃብት ልማትና ሥራ አፈጸጻም አመራር ቡድን ሲሆን የስልጠናው ዓላማ ለአዲስ ሰራተኞች የኮርፖሬሽኑን አጠቃላይ ገጽታ እና አሰራር ማስተዋወቅ ላይ ያተኮረ ነው፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የኮርፖሬት ሰው ሃብት ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት፣ የኮርፖሬት የህግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት፣ የኮርፖሬት ሥነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት እና የኮርፖሬት ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ሲሆኑ ከተለያዩ ዘርፎችና የስራ ክፍሎች የተውጣጡ ሰራተኞች በሥልጠናው ተካፍለዋል፡፡