Get Mystery Box with random crypto!

ኮርፖሬሽኑ የሲሚንቶ ምርት ሽያጭ በማካሄድ ላይ ይገኛል መንግስት ከሲሚንቶ ምርት ግብይት አኳያ የ | Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)

ኮርፖሬሽኑ የሲሚንቶ ምርት ሽያጭ በማካሄድ ላይ ይገኛል

መንግስት ከሲሚንቶ ምርት ግብይት አኳያ የሚታየውን ችግርና የዋጋ ንረት ለማረጋጋትና የምርት ስርጭቱን ቅደም ተከተል በማስቀመጥ ግብይቱን ግልጽና ተደራሽ ለማድረግ እንዲያስችል የአሰራር ስርዓት ዘርግቷል፡፡ በመሆኑም ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በተላከው የሲሚንቶ ምርት፣ ግብይትና ስርጭት መመሪያ መሰረት የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ለሲሚንቶ ምርት ፈላጊዎች ሽያጭ እያከናወነ ይገኛል፡፡

አስፈላጊውን መረጃ ላሟሉ ለመንግስት ግንባታ እና ለግል ገንቢዎች እንዲሁም ለብሎኬት አምራቾች ከነሐሴ 17/ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የሽያጭ ፕሮግራም ኮርፖሬሽኑ ያወጣ ሲሆን ተጠቃሚ የሚሆኑት ክፍለ ከተሞች ቂርቆስ፣ ልደታ፣ አዲስ ከተማ፣ ኮልፌ ቀራንዮ፣ ጉለሌ እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ናቸው፡፡ ከነሐሴ 17- 27/2014 ዓ.ም የቂርቆስ፣ የልደታ እና የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች ተጠቃሚ የነበሩ ሲሆን ከነሐሴ 28/ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ተጠቃሚ በመሆን ላይ ይገኛል፡፡ የጉለሌ እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች ደግሞ በመቀጠል በወጣላቸው ፕሮግራም መሰረት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡