Get Mystery Box with random crypto!

በመደበኛ ግዢ ላይ የተሰጠው ስልጠና ወቅቱን የጠበቀ መሆኑ ተገለጸ ከሐምሌ 9-13/ 2014 ዓ.ም | Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)

በመደበኛ ግዢ ላይ የተሰጠው ስልጠና ወቅቱን የጠበቀ መሆኑ ተገለጸ
ከሐምሌ 9-13/ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ቀናት በመደበኛ ግዢ ላይ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት አቶ ይርጋሸዋ ተሾመ የኮርፖሬት ህግ፣ ማህበራዊ ጉዳዮችና የአሰራር ዘዴ ማሻሻያ ም/ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንደገለጹት ስልጠናው የ2015 በጀት ዓመት የግዢ ስራ ከመጀመሩ በፊት መሰጠቱ ወቅታዊ ስልጠና ያደርገዋል፡፡ በስልጠናው ሰልጣኞች የኮርፖሬሽኑን የግዢ ሂደትና አፈጻጸም ያለበትን ችግር የተገነዘቡበት መሆኑን ገልጸው በቀጣይ አመራሩም ሆነ ሰራተኛው መሰል ስልጠናዎችን እየወሰዱ አቅማቸውን ማጠናከርና ተመሳሳይ ግንዛቤ መያዝ አለባቸው ብለዋል፡፡
ም/ሥ/ አስፈጻሚው አክለውም በግዢ አሰራር ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት የግዢ መመሪያ መጽደቁን ጠቁመው፣ ከተሰጠው ስልጠና ጋር በቂ ስንቅ በመሆኑ ሁሉም ለስራ ዝግጁ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ አያይዘውም ከግዢ ባለሙያዎች የሚጠበቁ ነገሮች በማለት ባስተላለፉት መልእክት የግዢ ባለሙያዎች የግዢን ዓላማ ማወቅና የግዢን ሂደት መገምገም ላይ ትኩረት አድርገው መስራት እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ በእቅድ የተመራ ጥራት ያለው ግዢ በመፈጸም ተደጋጋሚ ግዢን ማስቀረትና ኮርፖሬሽኑን ከአላስፈላጊ ወጪ ማዳን እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡
የስልጠናው ተሳታፊዎች ስልጠናው በብቁ ባለሙያዎች የተሰጠ እና ወቅቱን የጠበቀ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም ስልጠናውን ለተከታተሉት ተሳታፊዎች የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡