Get Mystery Box with random crypto!

በግዢ (Regular procurement) ላይ ያተኮረ ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል በግዢ (Reg | Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)

በግዢ (Regular procurement) ላይ ያተኮረ ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል

በግዢ (Regular procurement) ላይ ያተኮረ ስልጠና ከነሐሴ 9/ 2014 ዓ.ም ጀምሮ በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ስልጠናው በኮርፖሬሽኑ የሰው ሃብት ልማትና ሥራ አፈጻጸም አመራር ቡድን የተዘጋጀ ሲሆን የግዢና የማማከር አገልግሎት ንግድ ስራ ዘርፍ ደግሞ በዘርፉ ብቃትና ልምድ ያላቸውን አሰልጣኞች በመለየት ተሳትፏል፡፡ በስልጠናው ከ30 በላይ የሚሆኑ የኮርፖሬሽኑና በየዘርፉ የግዢ ሰራተኞች፣ የማዕከል ግዢ ቡድን አመራርና ሰራተኞች፣ የአቢይ የጨረታ ግዢ ኮሚቴዎች፣ የጨረታ ግዢ የቴክኒክ ኮሚቴ ጸሃፊና ሰብሳቢዎች እና የህንጻ ግንባታ ጥገና ባለሙያዎች በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡

ስልጠናው በኮርፖሬት የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት፣ በኮርፖሬት ሥነ- ምግባርና ጸረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት እና በኮርፖሬት የአሰራር ዘዴና የአገልግሎት ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት በኩል አስቀድሞ በጥናት የተለዩ የግዢ ችግሮችን ሊቀርፍ በሚችል አግባብ የተዘጋጀ ስለመሆኑ ተገልጿል፡፡ ስልጠናው ኮርፖሬሽኑ ለግዢ ከሚያውለው የገንዘብ መጠንና የሥራው አስፈላጊነት አንጻር ተገቢውን ሥልጠና በመስጠት በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት ማስቻል ዓላማውን አድርጓል፡፡

በስልጠናው Introduction to Purchasing- Basic Concept, Procurement Methods & INCOTERMS, Procurement Planning, Production of Tender Document የሚሉና ሌሎች ተዛማጅ ርእሰ ጉዳዮች ተካተዋል፡፡ ስልጠናው የተሻለ ጥራትና ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን ለአምስት ቀናት ይቆያል፡፡