Get Mystery Box with random crypto!

በእዉቀቱ ስዩም

የቴሌግራም ቻናል አርማ esubealem — በእዉቀቱ ስዩም
የቴሌግራም ቻናል አርማ esubealem — በእዉቀቱ ስዩም
የሰርጥ አድራሻ: @esubealem
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 961
የሰርጥ መግለጫ

ወዳጄ ሆይ ቀድመህ ከራስህ ጋር ታረቅ፤ቀጥለህ አዕምሮህን ወዳጅ አድርግ!
በመጨረሻም ከአለሙ ጋር ተስማምተህ መኖር የሚያስችልህን እዉቀት ና ልምድ ታገኛለህ።
✍...BE UR SELF
ለማንኛውም አስተያየት @Esubealembot
17/08/2013 E.C

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-07-30 20:13:11 አትፍረዱ አይፈረድባችሁምም፤አትኰንኑ አትኰነኑምም፤ይቅር በሉ ይቅርም ትባላላችሁ።
290 views17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 12:16:28 «እየው እጄ ሞቶ፤ እየው እግሬ ሞቶ
ያስለፈልፈኛል ሆዴ ብቻ ቀርቶ»


ሺህ ሰዎች ተሳስተው አንዱ ብቻ ልክ ሊሆን ይችላል ...
አዎን መቶ አህዮች ባንድነት ሲያናፉ ከአንድ መሲንቆ የተሻለ ጣዕም ሊኖራቸው አይችልም።


አሁንም ቢሆን እኔ የማምነው ከብዙ ምላስ በትንሽ ስራ ነው።
#ኢትዮጵያ እጆቿን ወደሰማይ ዘርግታ ፀሎት ስታደርስ በቀለም ትምህርት ናላው ሰክሮ በእጁ መስራት ከማይፈልግ ትውልድ አድነኝ ሰውረኝ ብላ መለመን አለባት።


አእምሮ ያሰበውን ያንን ስራ ላይ እጅ ማዋል አለበት።
በእጅ አማካይነት በስራ ያልተገለጠ ሃሳብ የማይታይ ፤ የጋን መብራት ሆኖ ይቀራል።
እርግጥ ዓለም በሃሳብ ባህር የሚዋኙ መለኮት የሚታያቸው ሰዎች ያስፈልጓታል።


ያለእነርሱ ወደፊት ልትራመድ አትችልም።


ይሁን እንጂ የአክሱም ሀውልቶችና የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት የታነፁት በህልም ብቻ አይደለም።


በእጅ ነው።


የፖለቲካ ፍልስፍናን በመለፈፍ ብቻ ኢትዮጵያን እናሻሽላለን ማለት ዘበት ነው።
የመንፈስ ደካማነት ምልክት ሊሆን ይችላል።


ምላስን ከማወናጨፍ ይልቅ እጅን ለትንሽ ስራ መዘርጋት የበለጠ ወኔን ፤ ቆራጥነትንና መስዋእትነትን ይጠይቃል።
አእምሮን የሚመራው እጅ ነው ማለቴ አይደለም።
እጅ ለስራ እንዲቃጣ የማያደርግ አእምሮ ህሊና ቢስ ነው።


እምነትና ድርጊት ከተለያዩ ምሠሶው በምስጥ እንደተበላ ቤት መዛግ ከዚያም መፍረስ ይመጣል - ወና ቤት መሆን።

[ የህሊና ደወል፦ከበዓሉ ግርማ ]


ቻናላችንን ለመቀላቀል @Esubealem
@Esubealem
328 views09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 11:56:55
ቻናላችንን ለመቀላቀል @Esubealem
@Esubealem
298 views08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 19:40:44 ም ኞ ት የ ኃ ጢ አ ት መ ሠ ረ ት ና ት !
334 views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 19:38:53 እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው ፤ ሕግም ነቢያትም ይህ ነውና።

[ የማቴዎስ ወንጌል 7:12 ]


ቻናላችንን ለመቀላቀል @Esubealem
@Esubealem
316 views16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 15:45:45 ሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ቀዳማዊ

"#ኢትዮጵያ_የኢትዮጵያውያን_ብቻ_ናት።"

በሁለተኛው የኢጣሊያ ወረራ ጊዜ -ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ ሐምሌ 22 ቀን1928 ተይዘው ወደ ግራዝያኒ ቀረቡ ወደ ችሎትም ሲቀርቡ. . .

እንዲህም አሉ፦

" አቡነ ቄርሎስ ግብፃዊ ናቸው፣ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውን የሚገዳቸው ነገር የለም።እኔ ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ ።ሃላፊነትም ያለብኝ የቤተ ክርስቲያን አባት ነኝ። ስለዚህ ስለ ሀገሬና ስለ ቤተ ክርስቲያኔ እቆረቆራለሁ፣ከዚህ በቀር ለእናንተ ችሎት የማቀርበው ነገር የለኝም ለፈጣሪዬ ብቻ የምናገረውን እናገራለሁ።"

* * *

" አረማዊ የሆነው የፋሽስት መንግሥት ቤተ ክርስቲያን ለማቃጠል ሕዝበ ክርስቲያንን ለመግደል ፣ሃይማኖትን ለማጥፋት ፣ታሪካችንን ለማበላሸት የመጣ ነው እንጂ በጎ ለመሥራት እውነተኛ ፍርድ ለመስጠት ስላልመጣ ለዚህ ግፈኛ አትገዙ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዚህ ጠላት እንዳይገዛ አውግዣለሁ ፣የኢትዮጵያ መሬት ጠላትን ብትቀበል የተረገመች፣ ትሁን።በፈጣሪዬ #በኢየሱስ_ክርስቶስ ስም የተገዘተች ትሁን" ብለው ካወገዙ እና ከገዘቱ በኋላ ፋሽስቶች ሊገሏቸው አቁመው

" ፊትዎን ለመሸፈን ይፈልጋሉ?" ሲሏቸው

"ይህ የእናንተ ሥራ ነው" ብለዋቸዋል።

ብፁዕነታቸው የተገደሉት መኻል አዲስ አበባ ዛሬ መታሰቢያ ሐውልታቸው ቆሞ በሚገኝበት አካባቢ ነው።

ደራሲና ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ ፦

"አቡነ ጴጥሮስ መጀመሪያ በእጃቸው ይዘውት የነበረውን መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ተሳለሙት፣ቀጥለውም በያዙት መስቀል አማትበው ሕዝቡን ባረኩ..." ብሏል

ብፁዕነታቸው ሐምሌ ፲፮ ቀን1938 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ እምብርት ሐውልት ቆሞላቸዋል ።

#ይህ_የእኛ_ኢትዮጵያውያን_ታሪክ_ነው ።


ቻናላችንን ለመቀላቀል @Esubealem
@Esubealem
319 views12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 15:45:30 ሰቆቃው ጴጥሮስ ግጥም

[ ሎሬት ፀጋዬ ገ/ መድህን ]


ቻናላችንን ለመቀላቀል @Esubealem
@Esubealem
279 views12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 15:43:39
273 views12:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 11:51:51
ናስሩዲን ከተከታዮቹ ጋር በአጀብ ሆኖ በአንድ የገበያ ስፍራ ያልፋል። ምንም ነገር ቢያደርግ ተከታዮቹ የሚያደርገውን ይደግማሉ። ጥቂት ራመድ ይልና እጆቹን ሰቅሎ ይወዘውዛል፣ ዝቅ ብሎ እግሮቹን ይነካል፣ ወደላይ እየዘለለም ይጮሃል። ተከታዮቹም እያንዳንዷን እንቅስቃሴ ሳያዛቡ ይደግማሉ።

ታዲያ አንድ ነጋዴ ወዳጁ " ምን እያደረክ ነው የዱሮ ጓዴ? እነዚህ ሰዎችስ ለምንድነው የምታደርገውን የሚያስመስሉት? " በሚል ይጠይቀዋል

"የሱፊ ሼክ ሆንኩ እኮ! እነዚህ ደግሞ መንፈሳዊነትን ለመለማመድ የተከተሉኝ ተማሪዎቼ ናቸው ። ወደ መንፈሳዊ አብርሆት ይሸጋገሩ ዘንድ እየረዳኋቸው ነው። " ናስሩዲን መለሰ።
ወዳጁ ግራ ተጋብቶ ጠየቀ። "አሃ! አብርሆት [Enlightenment] ላይ መድረሳቸውን በምን ታውቃለህ?

ናስሩዲንም " ያ ቀላል ነው። በየማለዳው ተከታዮቼን እቆጥራቸዋለሁ። ከሰልፉ የጎደሉት በርቶላቸዋል ማለት ነው!"


ቻናላችንን ለመቀላቀል @Esubealem
@Esubealem
291 views08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 11:19:43
ቻናላችንን ለመቀላቀል @Esubealem
@Esubealem
279 views08:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ