Get Mystery Box with random crypto!

ቻይና በጎበዝ አለቃ ተከፋፍላ 'ዘመነ መሣፍንት ' በመሰለ ዕጣ ፈንታ ታብታ በነበረበት ወቅት ነው። | በእዉቀቱ ስዩም

ቻይና በጎበዝ አለቃ ተከፋፍላ "ዘመነ መሣፍንት " በመሰለ ዕጣ ፈንታ ታብታ በነበረበት ወቅት ነው።

ኮንፊሺየስ የአንድነት አስተምህሮቱን በሥነ ምግባር አሽሞንሙኖ አቀረበ። የኮንፊሺየስ ደቀመዝሙር ሆኖ በቻይና ዕጣ ፈንታ የተነካ አንድ ተማሪ መምህሩ ፊት ቀረበ።

"ምን አሰብክ" ሲል ጠየቀ ኮንፊሺየስ

"አስተምህሮትህን ወደ ተጎራባች የጎበዝ አለቃ ግዛቶች፤ ማስፋፋት"

"አደገኛ ሥፍራ እንደሆነ ታውቅ የለም?"

"አዎ"

"ታድያ?"

"እቋቋመዋለሁ" በተማሪ ወኔ

"አይመስለኝም፤እስቲ አንዳንድ ጥያቄዎችን ላቅርብልህ"

"ይቀጥሉ መምህር ሆይ"


"ለመሆኑ ወደ ቺ ግዛት ስትገባ ቢያላግጡብህ ምን ታደርጋለህ?"


"ስላልመቱኝ አመሰግናቸዋለሁ "


"ጥሩ፣ ቢመቱህስ ?"

"ስላልገደሉኝ አመሰግናቸዋለሁ "


"ቢገድሉህስ?"

"ወደ ዘላለማዊው መገኛዬ የህይወት ባህር ስለቀላቀሉኝ አመሰግናቸዋለሁ"


"መሄድ ትችላለህ " አለ ኮንፊሺየስ።


. . .በስድብ የማረን ሊመታን የሚችለው ሰው ነው፤ በአካል ማጉደል የተወን ሰው የመግደል ዕድል በእጁ ላይ ያለች ባለጊዜ ነው. . .
:
:
:
ጠላት......ካደረገው በላይ እንዳያደርግ ማን አገደው. . .?

. . .አተራረፋችን በአምላካችን መሆኑ ቀረ እንዴ?. . .


ቻናላችንን ለመቀላቀል @Esubealem
@Esubealem