Get Mystery Box with random crypto!

#ቂሷ                              ክፍል-2 የ80 አመት አዛውንት አንድ የ80 | ⭐️ISLAMIC WORLD⭐️

#ቂሷ         
                    ክፍል-2
የ80 አመት አዛውንት

አንድ የ80 ዐመት አዛውንት ነበር 
እናም እሱ ምንም አይነት ቁርአን ኪታብ የሚባል ነገር ቀርቶ አያውቅም ነበር እድሜ ልኩን።

እናም ይሄ ሰውየ አንድ ቀን አሏህ ሽቶለት ቁርአን መቅራት አለብኝ ብሎ አሰበ በ80 ዐመቱ አሏህም ድፍረትን ሰጠውና ከልጅ ልጆቹ  ከህፃናቶቹ ጋር እየተመላለሰ መቅራት ጀመረ  እናም ህፃናቶች ይስቁበት ይቀልዱበት ነበር እሱም ያንሁላ ጫጫታ ቻል በማድረግ መቅራቱን ቀጠለ።

እናም ይህ ሰው አሏህ አግርቶለት ቁርዐንን ጨረሰ
ጨርሶም በቃኝ ብሎ አላቆመም ኪታብም መቅራት ጀመረ ሱብሀነሏህ ከዚያም ይሄን እድሜ ቸረውና 40 ዐመት ኪታብ ቀርቶ ጨረሰ አጠቃላይ እድሜው 120 ሆነ ማለት ነው።

አሁንም አሏህ ሰወችን እንዲያቀራ አገራለትና እንደሱ ዐይነት የነበሩ ሽማግሌወችን ሰወችን ወጣቶችን  ማቅራተ ጀመረ።

አሁንም አሏህ 40 ዐመት ጨመረለት 40 ዐመቱን በሙሉ በማቅራት ጨረሰው እናም ይሄ ሸይኽ 40  ዐመት በመቅራት 40 ዐመት በማቅራት አሳለፋት። እንደገና አዲስ የሆነ ሀያት ተሰጣቸው 80 አመት በጅህልና 80 አመት በእውቀት አሳለፋት። አጠቃላይ 160 ዕድሜ ነበር የኖሩት። ኻቲማቸው አምሮላቸው ወደ አኼራ ተጓዙ።
#ሱብሀነሏህ ምንኛ ያማረ ኻቲማ ነው። ኻቲማችንን አሏህ ያሳምርልነ


      ከዚ ቂሷ የምንረዳው
1 ገና ለገና እድሜያችን ሂዷል ብለን ቁርዐንን     
   ኪታብን መቅራት መተው እንደሌለብን

2 ሶብር በማንኛውም ግዜ ኢልምን ለመውሰድ   
   የሚያግዱ ነገሮችን በሶብር ማለፍን

3 ተምሮ ማስተማርን ያስረዳናል ይሄ ቂሷ

እናም የምላችሁ ቁርዐን ያልቀሩ እናት አባት እህት ወንድም ያለን ሰወች እንዲቀሩ የማድረግ ሀላፊነት አለብን!

https://t.me/Eslmnachin99