Get Mystery Box with random crypto!

የኔ አላህ አል_ወሊይ የኔ አላህ ወዳጅ እንዲሁም ረዳታችን ነው። አአንዳንዴ ስከፋ ብዙ አስብና | ᎷUᏚᎯᏰ™ Islamic Page

የኔ አላህ

አል_ወሊይ የኔ አላህ ወዳጅ እንዲሁም ረዳታችን ነው።
አአንዳንዴ ስከፋ ብዙ አስብና ሙስሊም ስለሆንኩ አላህዬ ስለመረጠኝና ስለወደደኝ በመንገዱ እንድመላለስ ሰለፈቀደልኝ ሁሉንም እረሳና ከልቤ ደስስ ይለኛል ምክኒያቱም የኔ አላህ ስንትና ስንት ለፀሀይ እና ጨረቃ ለእሳት ለጣኦታት ለተለያዩ ግዑዝ ነገራቶች የሚሰግዱና የሚያጎበድዱ ብዙሀኖች ባሉባት በዚች ጠፊ አለም ለኔ ግን ከሀይማኖት ምርጡ እስልምናን ሸለመኝ እሱን መገዛትን ለሱ ብቻ መስገድን ወፈቀኝ ምንምእንኳ ተገቢዉን መገዛት ባልገዛውም የሚገባዉ ያክል ሱጁድ ባላደርግም እሱ ግን ሁሌም ይወደኛል

መመረጤ በራሱ ጮቤ ያስረግጠኛል ሳልጠይቀው እንዳውቀው የለፈቀደልኝ ስለሚወደኝ አይደል ? እንዴታ! መንገዱን ሳልስት እንድገናኘው ጠይቄውማ አያሳፍረኝም ደግሞም ሙስሊምነት በራሱ ትልቅ ፈድል'ኮ ነው?!
ለዛም ነው አፌን ሞልቼ የኔ_አላህ ወዳጄ ረዳቴም ነው የምለው የኔ አላህ ከሚገባን በላይ ይወደናል በቀጥተኛው መንገዱም ላይ ፀንተን እንድንቆይ በተገቢውም ሁኔታ እንድንገናኘው ይረዳናል ምክኒያቱም እርሱ የሚወደን + የሚረዳን አል_ወልይ ነውና።

مَن يَه‍ْدِ اللَّهُ فَه‍ُوَ الْمُه‍ْتَدِۖ وَمَن يُضْلِلْ فَلَن تَجِدَ لَهُ وَلِيًّا مُرْشِدًا

አላህ የሚያቀናው ሰው ቅኑ እርሱ ብቻ ነው። የሚያጠመውመ ሰው ለርሱ አቅኝን ረዳት አታገኝለትም።
[አል_ካህፍ 17/١٧]

@Islamic_direction
@Islamic_direction