Get Mystery Box with random crypto!

ተማሪዎች ለመምህራኖቻቸው ምስጋና አቀረቡ ************** በባህር ዳር አቡነ ጎርጎርዮስ ቅ | Esdros S.C

ተማሪዎች ለመምህራኖቻቸው ምስጋና አቀረቡ
**************
በባህር ዳር አቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት የሚገኙ የአስራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች ለመምህራኖቻቸው የምስጋና መርሃ ግብር አዘጋጁ፡፡
ተማሪዎቹ መምህራኑ በእውቀት እና በሥነ-ምግባር አንጸው እዚህ ስላደረሷቸው ምስጋና ይገባቸዋል በሚል በራሳቸው ተነሳሽነት ባዘጋጁት በዚህ መርሃ ግብር ላይ ለሁሉም መምህራን ምስጋናቸውን አድርሰዋል፡፡
በመሆኑም በእለቱ በተማሪዎች በተደረገው ንግግር እናንተ በገሰጻችሁን ቁጥር ልጆች ነበርን እና ቢከፋንም ለኛ መሆኑን ተረድተን ከታች ድረስ ጀምረን እዚህ ስንማር ላደረጋችሁልን ከቃላት በላይ ለሆኑ መልካም ነገሮች በሙሉ ይህ ለናንተ ትንሽ ቢሆንም በጣም እናመሰግናለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
መምህራኑ በበኩላቸው በተማሪዎቹ በተዘጋጀው የምስጋና ጊዜ ላይ እስከ አሁን እንዲህ አይነት ልምድ ገጥሞን አያውቅም በማለት እጅግ እንደተደሰቱ በመግለጽ ከዚህ የበለጠ ዋጋ ከፍለን እንድናስተምር አነሳስታችሁናል ብሎም በቀሪው ጊዜ እናንተን በተሻለ መልኩ እናግዛለን ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ተማሪዎቹ ለትምህርት ቤታቸው የብጹህ አቡነ ጎርጎርዮስ ምስልን በትልቁ በማድረግ የሁሉም የአስራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች ስምን ከጀርባው በማስፈር ስጦታ አበርክተዋል፡፡ ከትምህርት ቤቱ ጋር ያላቸው ቆይታ በዚህ ዓመት የሚጠናቀቅ ቢሆንም እንደ ቤተሰብ ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ጋር አብረው የሚዘልቁ ይሆናል፡፡

የአክሲዮን ማህበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com/e/ በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ።