Get Mystery Box with random crypto!

33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነገ ይጀመራል!! በካሜሩን አስተናጋጅነት የሚካሄደው 33ኛው የአፍሪካ ዋን | Adey Drama - አደይ ድራማ

33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነገ ይጀመራል!!

በካሜሩን አስተናጋጅነት የሚካሄደው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነገ ይጀመራል፡፡ ውድድሩ ከጥር 1 ቀን እስከ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ካሜሩን አስተናጋጅነት ይካሄዳል፡፡

በዚህ ውድድር ላይ የሚሳተፉ 24 ብሔራዊ ቡድኖች አስቀድመው ወደ ካሜሩን አቅንተዋል፡፡በዚህ ውድድር ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ስፍራው ማቅናቱ ይታወሳል፡፡;የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት ፓትሪስ ሞሴፒ የነገውን ውድድር ለመክፈት ካሜሩን ገብተዋል፡፡

የውድድሩ መክፈቻ ፕሮግራም ነገ ምሽት ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን የመክፈቻ ጨዋታውን የውድድሩ አዘጋጅ አገር ካሜሩን ከኬፕቨርዴ ጋር ይደረጋል፡፡ከመክፈቻው ውድድር በኋላ ኢትዮጵያ ከኬፕቨርዴ ጋር ትጫወታለች፡፡ በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሁለተኛ ጨዋታውን ጥር 5 ቀን 2014 ዓ.ም ከውድድሩ አዘጋጅ አገር ካሜሩን ጋር ያደርጋል፡፡
@Esatethiopiantv
@Esatethiopiantv