Get Mystery Box with random crypto!

ኢሳት(ትኩስ ትኩስ ዜናዎች)

የቴሌግራም ቻናል አርማ esatchannal — ኢሳት(ትኩስ ትኩስ ዜናዎች)
የቴሌግራም ቻናል አርማ esatchannal — ኢሳት(ትኩስ ትኩስ ዜናዎች)
የሰርጥ አድራሻ: @esatchannal
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.81K
የሰርጥ መግለጫ

አዳዲስ ወሬዎችን ዜናዎችን ማግኝት ከፈለጉ እኛን ይቀላቀሉ ለወዳጅ ዘመዶ #share

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-06-10 20:24:41 በትግራይ ክልል ከሚገኙ አባቶች ጋር ውይይት ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጠናቀቁን ቅዱስ ሲኖዶስ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በግንቦት ወር 2015 ዓ.ም ባካሔደው የርክበ ካህናትጉባኤ በትግራይ ክልል ከሚገኙ አባቶች ጋር የሚደረገው ውይይት ቀደም ሲል በቋሚ ሲኖዶስ በተሰየመው የልዑካን ቡድን አማካኝነት በአስቸኳይ እንዲቀጥል መወሰኑ ይታወሳል።

በዚህም መሰረት የጠቅላይ ቤተክህነት ልዑካን ቡድን ውይይቱን ውጤታማ ለማድረግ ይቻል ዘንድ እስከ አሁን ያከናወናቸውን ተግባራትና ወደፊት ውይይቱን ስኬታማ በሆነ መንገድ ማካሔድ በሚችልበት ሁኔታ ዙሪያ ሰኞ ሰኔ 5 ቀን 2015ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ይፋዊ መግለጫ ይሰጣል።መግለጫውን ተከትሎም ጉዳዩ በቀኖና ቤተክርስቲያን መሰረት የመጨረሻ እልባት እንዲያገኝ በፍጥነት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በመግባት በሒደቱ የሚመዘገቡ ለውጦችን ሁሉ በመገናኛ ብዙሃን የሚያሳውቅ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
@esatchannal
6.5K viewsedited  17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 10:21:55
እስራኤል ወደ ጋዛ ሮኬቶችን ማስወንጨፍ ቀጥላለች

እስራኤል በጋዛ በፈፀመችው ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 21 ደርሷል።

በአየር ድብደባው 64 ሰዎች መቁሰላቸውን የፍልስጤም ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

የእስራኤል ጦር በበኩሉ ከጋዛ ሰርጥ 270 ሮኬቶች እና ሚሳኤሎች ወደ እስራኤል መተኮሳቸውን ገልጿል።

ከተተኮሱት ሚሳኤሎች ውስጥ 62ቱ ተመተው መውደቃቸውንም ነው የጦሩ ቃል አቀባይ የተናገሩት።

የእስራኤል ጦር 40 በሚሆኑ የምድር ውሰሰጥ የሚሳኤል ማስወንጨፊያዎችን መደብደቡንም አስታውቋል።


@esatchannal
1.4K viewsedited  07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 10:20:31
የኬንያ ፖሊስ ራሱን "እየሱስ ነኝ" ብሎ የሚጠራውን ግለሰብ ለማብራሪያ ጠራ

የኬንያ ፖሊስ ራሱን "እየሱስ ነኝ" ብሎ የሚጠራውን ግለሰብ ለማብራሪያ ጠራ።

ኢልዊድ ዌኬሳ በሚል ስሙ የሚጠራው ይህ ግለሰብ የአዲሷ እየሩሳሌም አዳኝ ነኝ በሚል ራሱን እየሱስ እንደሆነ በመናገር ላይ እንደሆነ ቢቢሲ ዘግቧል።

ዚህ ጉዳይ ምርመራ እያደረገ የሚገኘው የኬንያ ፖሊስ አሁን ደግሞ ራሱን እየሱስ ክርስቶስ እያለ የሚጠራን ግለሰብ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠይቋል።

በኬንያ አንድ ፓስተር አማኞች እየሱስ ክርስቶስን ለማግኘት እንዲጾሙ እና በረሀብ እንዲሞቱ አድርጓል በሚል በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል።

የፓስተር ፖል ማኬንዜ መልዕክትን ተቀብለው እየሱስን እናገኘዋለን በሚል ሲጾሙ ህይወታቸው ያለፉ ዜጎች ቁጥር እያሻቀበ ሲሆን ግለሰቡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራው እንደቀጠለ ነው ተብሏል
@esatchannal
1.3K viewsedited  07:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 04:35:13 ይህንን ብታነቡትና ለሌሎች ሼር ብታደርጉት ይጠቅማል

ጉዳዩ የአንድ ነጋዴ ገጠመኝ ይሁን እንጅ ብዙዎችን ያስተምራል።
<<ዛሬ ሱቄ ኣንድ ሰው ሞባይል ሊገዛ ይመጣል እናም ሲመጣ የቤት መኪና ፣ ህፃን ልጁንና ለመውለድ የተቃረበች ሚስቱን ይዞ ነበር። እናም ሚስቱን መኪናው ውስጥ አስቀምጧት ህፃን ልጁን ይዞ ወደ ሱቄ ይገባና iphone14 ስልክ ኣሳየኝ ብሎኝ ካሳየሁት በኃላ ዋጋውን ሲጠይቀኝ 165ሺ አልኩት እሱም እባክህ ሚስቴ ስላማራት ነው ቀንስልኝ ሲለኝ እሺ ብዬ 2ሺ ብር ስቀንስለት ተስማማን። ከዛም ባለቤቴን ከለር ላስመርጣት ብሎ ሶስት የተለያዩ ከለር ያላቸውን iphone 14 ስልኮች ልጁን ሱቄ ጥሎ ይዞ ወጣ። ያው እኔም ልጁን እዛው ስለተወና እርጉዝ ሴት ስላየሁ አምኘ ትኩረቴን ሌሎች ደንበኞች ላይ ኣደረኩኝ። ይመጣል ብዬ ብጠብቅ ምንም የለም።
ወጣ ብዬ ስመለከትም መኪናዋም እነሱም የሉም።ከዛ ወደ ሱቅ ተመልሼ ህፃኑን ስጠይቀው ከጎዳና ላይ ጠዋት አንስተውት ልብስ ገዝተውለት ፤ ፀጉሩን አሰሰተካክለው ፤ ገላውን አጣጥበው እንዳመጡት ነገረኝ ፣165x3=495ሺህ ብር ተበላሁ፣በጣም አዝኛለሁ>> ይላል ባለታሪኩ ነጋዴ ሲል አንድነት ናፍቆት አጋርቶኛል።ከመሰል አታላዮች ራሳችሁን ጠብቁ
@esatchannal
3.0K viewsedited  01:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 15:54:00 አጣዬ
" ከማረሚያ ቤቱ ካመለጡ ታራሚዎች የተወሰኑት በፍቃዳቸው ተመልሰዋል
አጣየ ማረሚያ ቤት በድጋሚ ወደ ስራ መግባቱንና ታራሚዎችን የመመለስ ስራ እየተሰራ መሆኑን የአጣየ ማረሚያ ቤት ጥበቃ መረጃ እና ደህንነት ቡድን መሪ የሆኑት ዋና ኢንስቴክተር ቁምላቸው ጌጤ ተናግረዋል ፡፡በአጣየ ማረሚያ ቤት በከተማው ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የተነሳ ማረሚያ ቤቱ በእሳት ተቃጥሎ እና ታራሚዎች ወደ መሃል ሜዳ ተዘዋውረው እንዲሁም የተወሰኑት አምልጠው የነበረ መሆኑ ተጠቁሟል ።

አያይዘውም በመሀል ሜዳ አንድ መቶ አስራ ስምንት ታራሚዎች ወደ ማረሚያ ቤቱ የተመለሱ ሲሆኑ ከነዚህም ዉስጥ አብዛኛዎች አምልጠው የነበሩ እና በፍቃዳቸው የተመለሱት እንደሚገኙበትም ተገለጿል።

በአጣየ ከተማ በአሁን ወቅት አንጻራዊ ሰላም ቢኖርም ወደ ቀደሞ የከተማዉ የንግድ እንቅስቃሴ ለመመለስ እየተሰራ እንደሚገኝም ተጠቁሟል/ዳጉ ጆርናል)

@esatchannal
4.7K viewsedited  12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 15:53:59 " ክስ ከተመሰረተብኝ እመለሳለሁ! " - አቶ ልደቱ አያሌው
#Ethiopia | መንግሥት በ "ሽብር ወንጀል እጠረጥራቸዋል" ያላቸውን በውጭ ሀገር ያሉና ተላልፈው እንዲሰጡ ማዘዣ ካወጣባቸው ግለሰቦች መካከል አንዱ የሆኑት ጉምቱው ፖለቲከኛ አቶ ልደቱ አያሌው "ክስ ከተመሠረተባቸው" ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ አሳውቀዋል።

አቶ ልደቱ እስካሁን ክስ እንዳልተመሠረተባቸው በጠበቃቸው እንደተነገራቸውና ክስ ከተመሠረተባቸው ግን ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመመለሱ ገልጸዋል።

ይህን የገለፁት ከቢቢሲ አማርኛ ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ ነው።

ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው ምን አሉ ?

"...ከጠበቃዬ ጋር እየተነጋገርኩ ነው። እስካሁን ክስ አልተመሠረተብኝም። ዝም ብሎ በራድዮና በቴሌቪዥን ይነገራል እንጂ የቀረበ ክስ የለም። ክስ ሲመሠረት ነው የምሄደው።

ክስ ከመመሥረቱ በፊት መሄዴ ጥቅም የለውም። በጊዜ ቀጠሮ መጉላላት ነው እንጂ ምንም ፋይዳ የለውም። እስከዚያ ድረስ ሕክምናዬን እከታተላለሁ /አቶ ልደቱ ለልብ ህመም በአሜሪካ የህክምና ክትትል ላይ ናቸው/ ።

ክስ ሲመሠረት ዳኞቹ የሚቀጥለው ሕክምናዬ ድረስ እንድቆይ የሚፈቅዱ ከሆነ እቆያለሁ። የማይፈቅዱ ከሆነም የሕክምና ቀጠሮዬን አቋርጬ እሄዳለሁ። "

አቶ ልደቱ ስለ ሽብር ክስ...

" የሕክምና ቀጠሮ ስለነበረኝ ነው እንጂ መጀመሪያም የመጣሁት እዚህ ለመኖር አይደለም። በቅርብ ጊዜ ወደ አገሬ እመለሳለሁ ብዬ እያሰብኩ ነበር። የዘገየሁት ያልተቋጨ የሕክምና ቀጠሮ ስለነበረኝ ነው። የሽብርተኛነት ክስ ሲመጣ ካሰብኩት ጊዜ ፈጥኜ ነው የምሄደው አልኩ።

የሕግ ተፈላጊነት ካለ፣በሽብርተኛነት የመጠየቅ ጉዳይ ካለ፣እኔ ከፍ/ቤት ውሳኔ እና ጥያቄ ርቄ መኖር ስለማልፈልግ ነው ለመሄድ የወሰንኩት።

...አገሪቱ ካለችበት ሁኔታ አንጻር ተመልሼ ለመውጣት ችግር ሊገጥም ይችላል ብዬ ነው እስካሁን የዘገየሁት። አሁንም የሕክምና ቀጠሮ አለኝ። ግን የሕግ ተጠያቂነት ከመጣ ምንም ማድረግ አይቻልም።

የተከሰስኩበት ወንጀል በፍጹም ከእኔ ታሪክ እና ማንነት ጋር የማይሄድ ነው። ሥርዓቱ ደግሞ ይሄንን ያደረገበት የራሱ ምክንያት አለው። አንደኛው ምክንያት እንደዚህ ዓይነት ክስ ፈርቼ ወደ አገሬ እንዳልመለስ ለማድረግ ስለሆነ ይሄንን በፈቃደኛነት ለመቀበል ዝግጁ አይደለሁም።

እኔ ሰላማዊ ታጋይ ነኝ። ሁልጊዜም በሕግ ነው የምተማመነው። ካሁን ቀደምም አምስት ስድስቴ ታስሬ በፍርድ ቤት ነው ነጻ የሆንኩት። አሁንም በዚያ መንገድ ሄጄ የግድ ሥርዓቱን መጋፈጥ አለብኝ በሚል ነው የምመለሰው።

ማናችንም ላለመታሰር፣ ዋጋ ላለመክፈል የየራሳችን ምክንያት ይኖረናል። ትግል ሲባል ግን እነዚህን ሁሉ ነገሮች ጥሶ መከፈል የሚገባውን ዋጋ መክፈል ነው።

ወደኢትዮጵያ ሲገቡ ስለሚገጥማቸው ችግር...

" ስሄድ የሚገጥመኝ ችግር ቀላል ነው ብዬ አይደለም። ከባድ እንደሚሆን አምናለሁ። ያ ችግር ምናልባት ሕይወቴንም ጭምር የሚያሳጣ ሊሆን ይችላል።

ግን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ፣ ሕዝቡ ያለበት ሁኔታ፣ ሰዎች በዚህ ደረጃ ዋጋ ለመክፈል ካልተዘጋጀንና ካልከፈልን ይለወጣል የሚል እምነት የለኝም። በእኔ ደረጃ ያለ ሰው ያን ዋጋ መክፈል እና ለትግሉ አርአያ መሆን አለበት ብዬ አምናለሁ።

ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ በፖሊስ ሊያዙ ስለሚችሉበት ሁኔታ...

" ልምዱ አለኝ። መታሰር የመጀመሪያዬ አይደለም። በዚህ ዓይነት ትግል ውስጥ ላለፉት 31 ዓመታት ቆይቻለሁ። ወደ 6 ጊዜ ስለታሰርኩ ለእኔ አዲስ ነገር አይደለም።

ከእኔ ጋር በመግለጫ የተጠቀሱ ግለሰቦች እየታደኑ እያተሰሩ እንደሆነ አውቃለሁ፤ ኤርፖርት የሚጠብቀኝ ፖሊስ እንደሚሆንና እንደምታሰር አውቃለሁ። ለዚህ የሥነ ልቦና ዝግጅት አለኝ።"
ቢቢሲ

@esatchannal
4.6K viewsedited  12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 15:51:44 ሰበር ዜና አሁን ፡ ከግምባር ምሬ ወዳጆ
አብይን የማስወገድ አዲሱ የህውሃት ሴራ
የጀኔራሉ ንግግር ሾልኮ ወጣ
ሀጫሉ ሁንዴሳ ፡ ልደቱ አያሌው
ሙሉ መረጃዉ



4.2K viewsedited  12:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 12:42:34 ምርጫ ቦርድ የትግራይ ክልልን ጨምሮ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች እና አአካባቢያዊ ምርጫን በ2016 ዓ.ም ለማካሄድ ማቀዱን አስታውቋል።

@esatchannal
4.6K viewsedited  09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 12:42:34
ፕሬዝዳንት ፑቲን “ምዕራባውያን ሩሲያን ለማጥፋት እየሞከሩ ነው” አሉ

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የሶቭየት ህብረትን የድል ቀን በማስመልከት ንግግር ያደረጉት ፑቲን "እውነተኛ ጦርነት" በሩሲያ ላይ በድጋሚ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።

ፑቲን አክለውም በፈረንጆቹ 1945 ሶቭየት ህብረት በናዚ ጀርመን ላይ የተቀዳጀውን ድል ምዕራባውያን ዘንግተውታል ብለዋል።

ፑቲን ሞስኮ የወደፊት ሰላምን ማየት እንደምትፈልግ ገልጸዋል(አልአይን)።

@esatchannal
4.6K viewsedited  09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 12:42:33 ሰሞኑን የትግራይ ታጣቂዎች እስከ ግንቦት 3 በሀይል ራያ አላማጣ እንገባለን በማለት ፕሮፖጋንዳ እየነዙ የነበረ ቢሆንም ጊዚያዊ አስተዳደሩ ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጋር ባደረግነው ውይይት መሰረት በርተክላይን መሳሪያ የያዘ ሰው አያልፍም የሚል ስምንት ላይ መድረሳቸውን ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል። የሚመለሱ ተፈናቃዮች ቢኖሩ እንኳን መሳሪያ ሳይዙ በርተኽላይን አልፈው መግባት እንደሚችሉ ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጋር ከስምምነት የተደረሰ ሲሆን ከዚህ ውጪ የሚደረግ የፕሮፓጋንዳ ሽብር አይጠቅምም ብለዋል።ትናንት በማይጨው ከተማ እና ገጠራማ አካባቢዎች ድሽቃ፣ብሬን እና ሞርታር የያዙ ታጣቂዎች መታየታቸውን ትናንት መዘገቤ ይታወሳል
@esatchannal
4.4K viewsedited  09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ