ሴኔጋል ለ2022 ዓለም ዋንጫ አለፈች።
የአፍሪካ ዋንጫ ባለድሏ ሴኔጋል በፍፃሜው ያገኘቻትን ግብፅን በድጋሚ በመለያ ምት በማሸነፍ ለኳታሩ 2022 ዓለም ዋንጫ ማለፏን አረጋግጣለች።
በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ሴኔጋል ካይሮ ላይ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፋ ነበር።
ዛሬ በሀገሯ ላይ በተካሄደው የመልስ ጨዋታ አንድ ጎል አስቆጥራ በመደበኛው እና ተጨማሪው ሰላሳ ደቂቃ በድምር ውጤት 1-1 ከተጠናቀቀ በኋላ ጨዋታው በመለያያ የፍፁም ቅጣት ምት በሴኔጋል 3-1 ውጤት ተጠናቋል።
ሴኔጋላዊው ኮከብ ማኔ በዓለም ዋንጫው ላይ የሚታይ ሲሆን ግብፃዊው ኮከብ ሳላህ በዓለም ዋንጫው ድንቅ ብቃቱን የሚያሳይበት ዕድሉ መክኗል።