Get Mystery Box with random crypto!

#እባክን_ትዝታ : : ትዝታን ሚያሸንፍ ትዝታን ሚበግር፤ ትዝታን ሚቀጣ ትዝታን የሚያስር፤ አንዳች | አንዳችን ለአንዳችን እናስፈልጋለን

#እባክን_ትዝታ
:
:
ትዝታን ሚያሸንፍ ትዝታን ሚበግር፤
ትዝታን ሚቀጣ ትዝታን የሚያስር፤
አንዳች በጠፋበት እስከዛሬ ደርሶ፤
በትካዜ ማንኪያ ያልጨለፈ አይኖርም ትናንትን መልሶ።
:
:
ትዝታ ረቂቅ ነው የዃሊት ይሰዳል፤
አንዳንዱን ያስቃል አንዳንዱን ያነዳል።
:
:
በሰመመን መንገድ የሰመመን ጉዞ፤
ሁለት አይነት ስሜት ሳቅና እምባን ይዞ።
:
:
እንዲ ነው ትዝታ እንዲ ነው ሰው ማሰብ፤
ትናንትን አስታውሶ ወይ መርገፍ ወይ ማበብ።
:
:
እናም እኔ ዛሬ...
ለማይቀረው እዳ ለዚ ለትዝታ፤
ተማፅኜዋለው ይውልልኝ እንደው ይህንን ውለታ።
:
:
ያሳብ ጀልባን ቀዝፈ፤
ሰመመንን ነድፈ፤
ልትውስደኝ ስትመጣ ካሳለፍኩት ማዶ፤
እንዳልብሰለሰል ውስጤ በግኖ ነዶ፤
መልካም ብቻ አሳየኝ መልካም የሆነን ሁሉ፤
እባክን ትዝታ እባክን አያሉ።


◆━━━━━━━✎✦✎━━━━━━━━◆

ሼር SHARE
  


@Eraza_fil
@Eraza_fil