Get Mystery Box with random crypto!

​ትዝታ ትዝታ እኮ ሳቅ ነው ቢኖረውም ትካዜ ትዝታ ታሪክ ነው የማይረሱት ጊዜ እኔም ኑሪያለሁ | አንዳችን ለአንዳችን እናስፈልጋለን

​ትዝታ


ትዝታ እኮ ሳቅ ነው ቢኖረውም ትካዜ
ትዝታ ታሪክ ነው የማይረሱት ጊዜ
እኔም ኑሪያለሁኝ በትዝታ አለም
ስለአንች በማሰብ ስለአንቺ በማለም
በሱ ድንቅ ውበትሽ ሁሌ በመገረም
መኖር ከተባለ እኔም ኑሪያለሁኝ
በዝምታ አለም ሁሌ እየፈራሁኝ
በአይናፋር አንደበት ዝምታን መርጨ
ከመናገር ይልቅ በሀሳብ ቀጭጨ
ፍቅሬን በመደበቅ ማውራትን ፈርቼ
በስቃይ ኑሪያለሁ ግራ ተጋብቼ
አንችኑ በመራብ
ስለአንቺ በማሰብ
ራሴን በመውቀስ ራሴን በመስደብ
በዚች አስቸጋሪ በዚች ፈታኝ አለም
በተመስጦ ታሪክ በሚመስል ህልም
እውነት ኑሪያለሁኝ አንቺኑ በማሰብ ስለአንች በማለም


◆━━━━━━━✎✦✎━━━━━━━━◆

ሼር SHARE
  
t.me/Eraza_fil

@Eraza_fil
@Eraza_fil