2022-11-21 16:48:37
የእናቶች እና ጨቅላ ህጻናት ሞት ቅኝት እና ምላሽ ስርዓትን በማስመልከት ለከፍተኛ የመንግስት እና የአጋር አካላት ኃላፊዎች የተዘጋጀዉን የማነቃቂያ መድረክ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባህልና ስፓርት ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የክልል ጤና ቢሮ እና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የስራ ኃላፊዎች፣ የአጋር ድርጅት ኃላፊዎች እና ተወካዮች እንዲሁም የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች በተገኙበት በዛሬዉ ዕለት አካሂደናል።
በዚህም መድረክ በወሊድ ምክንያት የሚከሰት የእናቶች እና የህጻናት ሞት ቅኝት እና ምላሽ አሰጣጥ (MPDSR) ዙሪያ ያሉትን አፈጻጸሞች እና ክፍተቶች በማየት ከዚህ ቀደም በተቀመጡ የመፍትሄ አቅጣጫዎች የጋራ ውይይት አድርገን ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠናል፡፡
“የእናቶች እና ጨቅላ ህጻናት ሞትን በፍጥነት በማሳወቅና ምላሽ በመስጠት በተመሳሳይ መንስኤዎች ምክንያት የሚከሰቱ የእናቶችና ጨቅላ ህፃናት ሞትን እንከላከል።”
“Protecting health and saving lives in outbreaks and emergencies!”
Facebook https://www.facebook.com/AschalewAW2020/
Twitter https://twitter.com/AschalewAbayneh?s=09
Telegram https://t.me/EPHI2O20
224 views13:48